አቢይ ርዕስ
የቴክኖሎጂ አበይት አጀንዳዎች፣ ፖሊሲዎች እና ርዕሰ ጉዳዮች ይተነተኑበታል።

የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ
ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ዜጎችን በክህሎትና በቴክኖሎጂ በማብቃት፣ የሀገሪቱን ምጣኔ ሀብት ወደ እውቀት መር ብልጽግና የሚያሸጋግር ግዙፍ ሀገራዊ የለውጥ ፍኖተ ካርታ ነው።

ቴክኖ-ፊውዳሎች ማዕቀብ ቢጥሉስ❓
የኢትዮጵያ ተቋማት በውጭ የAI ኤፒአይዎች ላይ ጥገኛ መሆናቸቸ ለውጭ ምንዛሬ እጥረት፣ ለመረጃ ደህንነት ስጋት እና ለድንገተኛ ጂኦፖለቲካዊ ማዕቀቦች ያጋልጣል። ይህ ጥገኝነት የሀገሪቱን የዲጂታል ኢኮኖሚ በአንድ ጀምበር ሽባ ሊያደርገው ይችላል። ስለሆነም እውነተኛ የዲጂታል ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ የሀገር ውስጥ የAI ሞዴሎች እና የክላውድ መሠረተ ልማቶችን ግንባታ ማፋጠን የዲጂታል ኪራይ አዙሪትን ሰብሮ ለመውጣት የሚቻልበት ብቸኛው ዘላቂ መፍትሔ ነው።

የፋይናንስ ዘርፉ ታላቅ 'አብዮት'
ባይናንስ የክሪፕቶ እና የባህላዊ የፋይናንስ ሥርዓትን (TradFi) ያዋሃደ 'አብዮታዊ. አገልግሎት በመጀመር ተጠቃሚዎች በማንኛውም ሰዓት በStablecoins ታዋቂ የአሜሪካ አክሲዮኖችንና ETFs ማገበያየት ጀምሯል።

የቴክኖሎጂ ባርነት" ወይም 'ዲጂታል ፊውዳሊዝም'
ዲጂታል ፊውዳሊዝም ጥቂት ግዙፍ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች የክላውድ እና የ-AI መሠረተ-ልማቶችን በብቸኝነት በመቆጣጠር ዓለምን የዲጂታል ጭሰኛ ያደረጉበት ሥርዓት ነው። ተጠቃሚዎች (ግለሰቦች፣ ተቃማት እና ሀገራት) የእነሱን መተግበሪያዎች እና APIs ከመጠቀም ውጭ ሌላ አማራጭ የሌላቸው በመሆናቸው የባንክ እና የብሔራዊ ደህንነት መረጃዎቻቸውን ለባዕድ ሰርቨሮች አሳልፈው በመስጠት የዲጂታል ሉዓላዊነት ስጋት ላይ ወድቀዋል።

የላቁ የAi ሞዴሎች ለምን ይታገዳሉ?
ChatGPT 5.6 እና Claude Fable 5 የመሳሰሉ የላቁ የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ሞዴሎች ይፋ በሆኑ ማግስት ጥብቅ እገዳ የሚጣልባቸው በሁለት ዋና ዋና ምክንያቶች ነው። የመጀመሪያው የሳይበር ደህንነት ስጋት ነው። ሞዴሎቹ የሲስተም ክፍተቶችን በሰከንዶች ውስጥ በመለየት ወሳኝ መሠረተ ልማቶችን የሚያሰናክሉ የጥቃት ኮዶችን በራሳቸው የመጻፍና ራሳቸውን ችለው ጥቃት የማሰንዘር አቅም አላቸው። ሁለተኛው የባዮ-ምርምር ስጋት ደግሞ ገዳይ ቫይረሶችን ይበልጥ ተላላፊና ለክትባት የማይበገሩ የማድረግ ብቃት ስላላቸው እና ላልሰለጠኑ አጥፊዎች ጭምር አደገኛ የባዮሎጂካል መርዝ አዘገጃጀት መመሪያዎችን ማቅረብ የሚያስችሉ በመሆናቸው ነው። ይህ አደጋ ክፉዎች እጅ ከገባ በመላው ዓለም ስጋት ሚጋርጥ ማገድ እንደ መፍትሄ ተወስዳል።
