ስለ እኛ · About

መጪውን ዘመን የሚቀርጹ ቴክኖሎጂ ነክ መረጃዎችን እናጋራለን።

ሰው ሰራሽ አስተውሎት እና ቴክኖሎጂን ከማወቅ ባለፈ አዳዲስ ክህሎቶችን በመቅሰም የፈጠራ አቅምዎን የሚያሳድጉበት እና ተጠቃሚነትዎን የሚያጠናክሩበት አስተማማኝ የእውቀት ማዕከል ይሆናል።

የዘርፉን ምሁራዊ እይታዎች እና ጥልቅ ትንተናዎች፣ ተግባራዊ መመሪያዎች እና ስልጠናዎች፣ ገለልተኛ ግምገማዎች እና ዳሰሳዎች፣ የተመረጡ ዜናዎች እና ለዘርፉ ችግሮች መፍትሄዎችን እናቀርባለን።

Stay ahead of the tech curve.

ዓላማችን · Our Aims

በአገር በቀል ቋንቋዎች የሰው ሰራሽ አስተውሎት እና ቴክኖሎጂ ነክ የእውቀት እና የክህሎት ክፍተትን መሙላት

በአገራዊ የዲጂታል ሽግግር ሂደት ጉልህ አስተዋጽኦ ማበርከት

የዘርፉ ባለድርሻዎች፣ አጋሮች፣ ተጠቃሚዎች፣ ስራ ፈጣሪዎች፣ ምሁራን፣ ተማሪዎች ያካተተ ጠንካራ ማህበረሰብ መገንባት

የዘርፉ ፖሊሲ እና ስትራቴጂ ገለልተኛ ጥናት እና ትንተና ማካሄድ፣ መፍትሄ እና ምክረ ሀሳብ ማቅረብ

What We Stand For

ተልእኳችን

ግለሰቦች እና ተቋማት ተጠቃሚነታቸውን አሳድገው ህይወታቸውን እንዲቀይሩ እና ለዘርፉ እድገት አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ ማስቻል ነው። ውስብስብ የሆኑ የሰው ሰራሽ አስተውሎት እና ቴክኖሎጂ ነክ መረጃዎችን ቀላል፣ ግልጽ እና ተግባራዊ በሆነ መንገድ በማቅረብ ተጠቃሚዎች የቴክኖሎጂ ውጤቶችን ለስኬታቸው እንዲጠቀሙባቸው ማስቻል ነው።

ራእያችን

በኢትዮጵያ አቆጣጠር በ2030 የዘገባ ሽፋኑን ወደ አምስት የአገር ውስጥ ቋንቋዎች በማሳደግ በአፍሪካ ቀንድ ግንባር ቀደም ተፅዕኖ ፈጣሪ እና ተመራጭ የቴክኖሎጂ፣ የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) እና የዲጂታል እውቀት ምንጭ መሆን ነው።

ዕሴቶቻችን

  • እውነተኝነት እና ጥራት
  • ገለልተኝነት እና ትብብር
  • ትስስር
  • ተደራሽነት

መነሻችን እና ግባችን

Alltechup የተነሳው ከአንድ ቀላል ምልከታ ነው፤ በኢትዮጵያ ያለው የሰው ሰራሽ አስተውሎት እና የቴክኖሎጂ ሥነ-ምህዳር በፈጠራ ሥራዎች የተሞላ ቢሆንም የዘርፉ መረጃዎች ጥልቀት እና ስፋት ባለው አግባብ በአገር ውስጥ ቋንቋዎች ተደራሽ አይሆኑም። በዚህ ምክንያት በጣም ሰፊ የአጠቃቀም እና የግንዛቤ ክፍተት አለ።

ክፍተቱን መሰረት በማድረግ በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያዎች ማጋራት የጀመርናቸው የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) እና ቴክኖሎጂ ነክ ዜናዎች፣ ትንተናዎች እና እይታዎች በአጭር ጊዜ ውስጥ ሰፊ አመኔታ እና ተቀባይነት በማግኘታቸው ወደ ድረገጽነት አሳድጎ በተደራጀ እና ዘላቂነት ባለው መልኩ ማስቀጠል አስፈላጊ ሆኖ አግኝተነዋል።

ድረ-ገጻችን በአገር በቀል የቴክኖሎጂ ማህበረሰቦች እና በዓለም አቀፉ ሥነ ምህዳር መካከል ድልድይ ማገልገል በሚያስችል አግባብ የተዋቀረ ነው። በአቅም ውስንነት ምክንያት ለጊዜው በአማርኛ ቋንቋ ድረገጽን ከተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች ጋር በማቀናጀት የምንጀምረው ቢሆንም በሂደት በተለያዩ የአገር ውስጥ ቋንቋዎች እና በፖድካስት ጭምር ተደራሽ እናደርገዋለን።

መነሻችን እና ግባችን ተራ የመረጃ ማሰራጫ መሆን ብቻ አይደለም፤ የዘርፉ ማህበረሰብ መድረክም መሆን ነው። የሰው ሰራሽ አስተውሎት እና ቴክኖሎጂ ስለ ምርቶች እና አገልግሎቶች ብቻ ሳይሆን ስለ ሰዎች፣ ማህበረሰቦች እና ስለ ፈጠራ ሁለንተናዊ የለውጥ ኃይል እንደሆነ እናምናለን።

ማህበረሰባችንን ይቀላቀሉ

የቅርብ ጊዜ የሰው ሰራሽ አስተውሎት እና ቴክኖሎጂ ነክ ታሪኮችን ይከታተሉ፤ ከባለፈጠራዎች፣ ከሥራ ፈጣሪዎች፣ ከባለድርሻዎች እና ከቴክኖሎጂ አፍቃሪያን ጋር ይገናኙ።

Addis Ababa, Ethiopia · info@alltechup.com

Subscribe to our Newsletter

Subscribe to our email newsletter to get the latest posts delivered right to your email.

Pure inspiration, zero spam ✈️