አቢይ ርዕስ

የቴክኖሎጂ ባርነት" ወይም 'ዲጂታል ፊውዳሊዝም'

ADMIN on June 24, 2026

1 read
አቢይ ርዕስ

ዲጂታል ፊውዳሊዝም ጥቂት ግዙፍ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች የክላውድ እና የ-AI መሠረተ-ልማቶችን በብቸኝነት በመቆጣጠር ዓለምን የዲጂታል ጭሰኛ ያደረጉበት ሥርዓት ነው። ተጠቃሚዎች (ግለሰቦች፣ ተቃማት እና ሀገራት) የእነሱን መተግበሪያዎች እና APIs ከመጠቀም ውጭ ሌላ አማራጭ የሌላቸው በመሆናቸው የባንክ እና የብሔራዊ ደህንነት መረጃዎቻቸውን ለባዕድ ሰርቨሮች አሳልፈው በመስጠት የዲጂታል ሉዓላዊነት ስጋት ላይ ወድቀዋል።

የቴክኖሎጂ ባርነት" ወይም "ዲጂታል ፊውዳሊዝም" ዘመናዊውን የዲጂታል ዓለም በመካከለኛው ዘመን ከነበረው የመሬት ከበርቴዎች (ፊውዳሎች) እና የጭሰኞች ግንኙነት ጋር በማነጻጸር የሚገልጽ ፅንሰ-ሀሳብ ነው።

በመካከለኛው ዘመን ፊውዳሎች መሬቱን በብቸኝነት ይቆጣጠሩ ነበር፤ ጭሰኞች ደግሞ መሬት ስላልነበራቸው በፊውዳሎች መሬት ላይ ላባቸውን አንጠፍጥፈው የሚገኘውን ምርት ለጌቶቻቸው ያስረክቡ ነበር።

በዘመናዊው የዲጂታል ዘመን ደግሞ መሬቱ በ"ክላውድ እና በAI መሠረተ-ልማቶች" ተተክቷል። ጥቂት የማይባሉ ግዙፍ የአሜሪካ እና የቻይና የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች (Google፣ Microsoft፣ OpenAI፣ Amazon፣ Apple ወዘተ) የዲጂታል ዓለም ፊውዳሎች ሆነዋል።

ይህም የሆነው የAI ሞዴሎችን ለማልማት እና መረጃዎችን ለማቀናበር እጅግ ግዙፍ ሱፐር ኮምፒውተሮች፣ ከፍተኛ መዋእለ ንዋይ እና የተራቀቁ መሠረተ ልማት የሚጠይቅ በመሆኑ ነው:: በዚህ ምክንያት እነዚህን መሠረተ-ልማቶች መገንባት የሚችሉት ደግሞ ጥቂት በሀብት የናጠጡ ኩባንያዎች (ዲጂታል ከበርቴዎች) ብቻ ሆነዋል።

ስለሆነም ግለሰብ ተጠቃሚዎች፣ ተቋማት/ስታርትአፖች እና በርካታ አገራት "ዲጂታል መሬት" ስለሌለን ልክ እንደ ጭሰኛ ገበሬዎቹ የእነሱን መተግበሪያዎች እና APIs ለመጠቀም ተገድደናል። በነጻ ወይም በክፍያ የእነሱን APIs እና መሠረተ-ልማት ለመጠቀም የምናስገባው መረጃ በሙሉ በእጃቸው ያስገባሉ። መረጃዎን ተጠቅመውም የራሳቸውን የAI አእምሮ የበለጠ ያበለጽጋሉ። በሀብትም ይበልጥ ይበለጽጋሉ።

በአጠቃላይ ጥቂት ግዙፍ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች የክላውድ እና የ-AI መሠረተ-ልማቶችን በብቸኝነት በመቆጣጠር የተጠቃሚዎችን (የግለሰቦችም ሆነ የሀገራትን) መረጃ/Data ያለገደብ የሚበዘብዙበት አደገኛ የዲጂታል ፊውዳሊዝም ሥርዓት ፈጥረዋል።

ይህንን ሥርዓት ይበልጥ አሳሳቢ እና አደገኛ የሚያደርጉት የቴክኖሎጂ ፊውዳል ስርዓት የዓለምን የሃብት እና የሥልጣን ሚዛን በጥቂት የቴክኖሎጂ ቢሊየነሮች እጅ የሚያከማች በመሆኑ ነው። በዚህ ዘመን የእነዚህ ፊውዳሎች ቴክኖሎጂን አለመጠቀም የማይቻል በመሆኑ ሀገራት 'ሉዓላዊነታቸውን" ገላልጠው ከመስጠት የተሻለ አማራጭ አጥተዋል። የባንክ፣ የጤና እና የብሔራዊ ደህንነት መረጃዎቻቸውን ሳይቀር ለባዕድ ኩባንያዎች ሰርቨር ተጋልጠዋል።

A

Written by

ADMIN

Tech Analyst.

Keep Reading

ዜና ቴክ

ADMIN on August 12, 2026

OpenAI በሊኑክስ መጠቀም የሚያስችል የChatGPT መተግበሪያ አስተዋወቀ

OpenAI የሊኑክስ (Linux) ተጠቃሚዎችና ፕሮግራመሮች ሲያቀርቡት ለቆዩት ተደጋጋሚ ጥያቄ ምላሽ በመስጠት አዲስ የChatGPT ዴስክቶፕ መተግበሪያ በሙከራ ደረጃ (preview) አስተዋወቀ። ይህ መተግበሪያ ChatGPT፣ ChatGPT Work እና Codexን በዋና ዋና የሊኑክስ ስርጭቶች ማለትም Ubuntu፣ Debian እና Fedora በመሳሰሉት ላይ ለመጠቀም ያስችላል። ተቀናቃኙ Anthropic የClaude መተግበሪያን ለሊኑክስ ከለቀቀ ከአንድ ወር በኋላ OpenAI ተመሳሳይ እርምጃ በመውሰድ ገበያውን ተቀላቅሏል።

ዜና ቴክ

ADMIN on August 12, 2026

ጉግል የGemini መተግበሪያ ተጠቃሚዎቹ ቁጥር ወደ 1 ቢሊዮን መድረሱን አስታወቀ

Gemini ai መተግበሪያ ከ1 ቢሊዮን በላይ ወርሃዊ ንቁ ተጠቃሚዎቹ ያሉት 14ኛው የድርጅቱ ግዙፍ ምርት መሆኑን ጉግል አስታወቀ። በተጨማሪም በiOS ላይ 100 ሚሊዮን ተጠቃሚዎች ሲኖሩት ከChatGPT ጋርም እኩል እየተፎካከረ ይገኛል።

ዜና ቴክ

ADMIN on July 25, 2026

AgentAi የፈጸመው አነጋጋሪ ተግባር

OpenAI በተናጠል አካባቢ (isolated environment) ሲሞክረው የነበረው የAI ኤጀንት፣ የሚፈልገውን መረጃ በማጣቱ በራሱ ውሳኔ ከተወሰነበት ገደብ ወጥቶ የHugging Faceን ድረ-ገጽ በመስበር (hack በማድረግ) መረጃ ወስዷል። የOpenAI ሥራ አስፈጻሚ ሳም አልትማን ኤጀንቱ ከቁጥጥር ውጭ ሆኖ ጥቃቱን ማድረሱን አምነዋል። ይህ ክስተት የባለሙያዎችን ስጋት እንዲጨምር አድርጎታል፤ ራሳቸውን ችለው የሚሰሩ ኤአይ ኤጀንቶች አቅም ማደጉ እና ቁጥጥር ማድረግ እየከበደ መምጣቱን አመላካች ተደርጎ ተወስዷል።

Subscribe to our Newsletter

Subscribe to our email newsletter to get the latest posts delivered right to your email.

Pure inspiration, zero spam ✈️