የላቁ የAi ሞዴሎች ለምን ይታገዳሉ?
አቢይ ርዕስ ⭐ Featured Story

የላቁ የAi ሞዴሎች ለምን ይታገዳሉ?

Written byADMIN
PublishedJune 30, 2026
Read Time5 min Read

ChatGPT 5.6 እና Claude Fable 5 የመሳሰሉ የላቁ የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ሞዴሎች ይፋ በሆኑ ማግስት ጥብቅ እገዳ የሚጣልባቸው በሁለት ዋና ዋና ምክንያቶች ነው። የመጀመሪያው የሳይበር ደህንነት ስጋት ነው። ሞዴሎቹ የሲስተም ክፍተቶችን በሰከንዶች ውስጥ በመለየት ወሳኝ መሠረተ ልማቶችን የሚያሰናክሉ የጥቃት ኮዶችን በራሳቸው የመጻፍና ራሳቸውን ችለው ጥቃት የማሰንዘር አቅም አላቸው። ሁለተኛው የባዮ-ምርምር ስጋት ደግሞ ገዳይ ቫይረሶችን ይበልጥ ተላላፊና ለክትባት የማይበገሩ የማድረግ ብቃት ስላላቸው እና ላልሰለጠኑ አጥፊዎች ጭምር አደገኛ የባዮሎጂካል መርዝ አዘገጃጀት መመሪያዎችን ማቅረብ የሚያስችሉ በመሆናቸው ነው። ይህ አደጋ ክፉዎች እጅ ከገባ በመላው ዓለም ስጋት ሚጋርጥ ማገድ እንደ መፍትሄ ተወስዳል።

የላቁ የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ሞዴሎች መንግስታት እና የደህንነት ተቋማትን የሚያስጨንቁበት እና እንቅልፍ የሚነሱበት ደረጃ ላይ ደርሰዋል። በዚህ ምክንያት የተለያዩ ህጎችን ከማውጣት ጀምሮ በሞዴሎች ጥብቅ እገዳዎችንም እየጣሉ ይገኛሉ። የበርካታ መንግስታት እና የደህንነት ተቋማትን የእገዳ ከተጣለባቸው መካከል የClaudeው Fable 5 የተሰኘ ሞዴል ተጠቃሽ ነው። ይፋ በተደረገ ማግስት ነበር መጠነ ሰፊ እገዳ የተጣለበት። ከትናንት በስቲያ ይፋ የተደረገው ሦስት ሞዴሎች ያሉት ChatGPT 5.6 (ChatGPT 5.5 update/ዝመና) ደግሞ የአሜሪካ መንግስት በየትኛውም አገር ለህዝብ አገልግሎት እንዳይውል እገዳ ጥሎበታል። ይህ ሞዴል ከClaude Fable 5 ሞዴል በእጅጉ የላቀ እንደሆነ ተነግሮለታል።

ይህ እገዳ በAi ሞዴሎች ልህቀት ምክንያት በመንግስታት እና በደህንነት ተቋማት እንዲሁም በመላው የዓለም ህዝብ ላይ ሁለት አሳሳቢሽ ተግዳሮቶች መጋረጣቸው ተከትሎ የመጣ ነው::

እነዚህም:-

1. የሳይበር ደህንነት ስጋት

አንድ የAI ሞዴል በዚህ ዘርፍ "ከፍተኛ አቅም አለው" ሲባል ፋይዳው የኮምፒውተር ሲስተሞችን መጠበቅ ብሎም የላቁ ተግባራትን ማከናወን ብቻ አይደለም። የመጥለፍ (Hacking) እና የማጥቃት ብቃቱ የላቀ ነው ማለትም ነው። የAi ሞዴሉ በሚሊዮን የሚቆጠሩ የኮድ መስመሮችን በአንድ ጊዜ በማንበብ የሰው ልጅ ባለሙያ በቀላሉ ሊያገኛቸው የማይችላቸውን የደህንነት ክፍተቶች (Zero-day vulnerabilities) በጥቂት ሰከንዶች ውስጥ ማግኘት ይችላል።

የተገኙትን ክፍተቶች ተጠቅሞ የኮምፒውተር ሲስተሞችን ወይም የአንድ ሀገር ወሳኝ መሠረተ ልማቶች (እንደ መብራት፣ ውሃ፣ ባንክ፣ ወታደራዊ . . .) ሊያሰናክሉ የሚችሉ የቫይረስ ኮዶችን በራሱ መጻፍ መቻሉም አደጋውን ግልጽ እና ተጨባጭ ያደርገዋል።

በልብ ወለዱ ዓለም በስፋት እንደሚታወቁት "ሶል አልትራ" የመሰሳሰሉ ኤጀንቶች የሰው ልጅ ትዕዛዝ ሳይጠብቁ ራሳቸው አቅደው፣ መርምረውና የሳይበር ጥቃት ሰንዝረው የተፈለገው ሲስተም የመቆጣጠር አቅማቸው የላቀ ነው። የሳይበር ጥቃቶችን በከፍተኛ ፍጥነት ማካሄድ ይችላል ማለት ነው።

2. የባዮ-ምርምር ስጋት

ይበልጥ ዓለምን እያስጨነቀ ያለው ይህ ስጋት ነው። ምክንያቱም ከሳይንሳዊ ምርምር አልፎ ወደ ባዮሎጂካል መርዞች እና ተላላፊ በሽታዎች (Bioweapons) የሚያመራ አደገኛ አቅም አለው።

ሞዴሉ በጂኖሚክስ እና ባዮሎጂ ላይ ባለው ከፍተኛ እውቀት ነባር የቫይረስ እና የባክቴሪያ መዋቅሮችን ይበልጥ ተላላፊ፣ ለክትባት የማይበገሩ ወይም ገዳይ አድርጎ የማሻሻያ መንገዶችን የመስራት አቅም አለው።

በተመሳሳይም አንድ ክፉ አላማ ያለው አካል/ሰው የሳይንስ እውቀቱ ሳይኖረው፣ አደገኛ የሆኑ ባዮሎጂካል ቁሶችን በምስጢር እንዴት ማዘጋጀት እና ማደባለቅ እንደሚቻል ደረጃ በደረጃ የሚያሰለጥኑ መመሪያዎችን ማዘጋጀት መቻላቸው ለእገዳ አጋልጧቸዋል።

በአጠቃላይ እነዚህና መሰል ሞዴሎች ክፉዎች እጅ ላይ ከወደቁ መላውን ዓለም ለአደጋ የሚያጋልጥ የሳይበር ደህንነት አደጋ፣ የጦር መሳሪያ ወይም ተላላፊ በሽታ መስሪያ እንዳይውሉ ማገድ እንደመፍትሄ ተወስዷል። እነዚህ ሞዴሎች ህዝብ አገልግሎት እንዳይሰጡ የሚታግዱ ከሆነ መጀመሪያውኑ ከፍተኛ በጀት አውጥቶ መስራቱ ለምን አስፈለገ?" የሚለው ጥያቄ ተደጋግሞ እየተነሳ ነው።