
"Sora" የተሰኘው የOpenai ቪዲዮ መተግበሪያ ተዘጋ
OpenAI በቀን $15 ሚሊዮን የሚፈጀውን Sora መተግበሪያ ዘጋ፤ የቪዲዮ ቴክኖሎጂውን ወደ “Spud” ለማዛወር እየሰራ ነው። ትኩረቱም ከቫይራል ቪዲዮ ይልቅ ለድርጅቶች ምርታማነትና ለወኪል AI (Agentic AI) ይሆናል።
ኦፕን ኤአይ (OpenAI) "Sora" የተሰኘው ተወዳጅ የቪድዮ መተግበሪያ ለጊዜው አገልግሎት ማቆሙን አስታወቀ።
ምንም እንኳን ቴክኖሎጂው ከፍተኛ ዝና ቢያተርፍም የሚጠይቀው በቀን እስከ 15 ሚሊዮን ዶላር ወጪ ከሚያስገኘው ገቢ በላይ መሆኑ በጊዝያዊነት ለመዝጋት መገደዱን አሳውቋል።
ይሁንና OpenAI የቪዲዮ ቴክኖሎጂውን "Spud" በሚል የኮድ ስም ወደሚጠራው የቀጣይ ትውልድ ሞዴሉ እያዛወረው እንደሆነ ሲጨርስ መልሶ ወደ አገልግሎት እንደሚያስገባው ገልጿል።
ይህ አዲሱ ሞዴል ትኩረቱን በቫይራል ቪዲዮዎች ላይ ሳይሆን በተቋማት ምርታማነት እና በተለያዩ ዘርፎች (multimodal) የማመዛዘን ብቃት እንዲኖረው የሚያደርግ ይሆናል።
ዘገባዎች እንደሚያመለክቱት OpenAI ትኩረቱን ከመገናኛ ብዙሃን መሳሪያነት ወደ ወኪል AI (Agentic Reasoning) የሚያስቀይረው ከመሆኑም በላይ አሁን ያለውን ወጪ በከፍተኛ ደረጃ መቀነስ እንደሚያስችለው ታውቋል።
አዲሱ "Spud" የተሰኘ የቀጣይ ትውልድ ሞዴል በቴክኖሎጂው ማህበረሰብ ውስጥ ለGPT-5 ተተኪ ሞዴል የተሰጠ የኮድ ስም እንደሆነ ይታመናል።
Comments (0)
Join the Conversation
Share your insights and connect with other readers by signing in.



