
በሰው ሰራሽ አስተውሎት ምክንያት ከ1000 በላይ ሰራተኞች ተቀነሱ
ስናፕ (Snap) መደበኛ ስራዎችን በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) በመተካቱ ከ1,000 በላይ ሰራተኞችን ቀነሰ
📱 ስናፕ (Snap) መደበኛ ስራዎችን በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) በመተካቱ ከ1,000 በላይ ሰራተኞች መቀነሱን አስታወቀአስታወቀ።
ስናፕ ከ1,000 በላይ ሰራተኞቹን (ከጠቅላላ ሰራተኞቹ 16 በመቶ ያህሉን) ማሰናበቱን ዛሬ ሲገልጽ ከ300 በላይ የስራ መደቦች እንደሚዘጋም አስታውቋል። ይህ እርምጃ የተወሰደው 2.5 በመቶ ድርሻ ባለው አይሬኒክ ካፒታል (Irenic Capital) የተባለ አክቲቪስት ባለሀብት ግፊት እንደሆነ ተጠቁሟል።
ኩባንያው እንደገለጸው ከሆነ፦
በአሁኑ ወቅት ከ65% በላይ የሚሆነው አዲስ ኮድ (code) የሚመረተው በAI አማካኝነት ነው።
ይህ መሆኑ አነስተኛ ቁጥር ያላቸው ቡድኖች ዋና ዋና ስራዎችን እንዲያከናውኑ ለማድረግ አስችሏል።
ስናፕ በዚህ የሰራተኛ ቅነሳ እስከ 2026 ሁለተኛ አጋማሽ ድረስ በዓመት ከ500 ሚሊዮን ዶላር በላይ ወጪ ለመቆጠብ አቅዷል።
ይህ የሰራተኛ ቅነሳ የተደረገው ስናፕ እንደ AR glasses (የaugmented reality መነጽሮች) በመሳሰሉ ምርቶች ላይ ኢንቨስት ማድረጉን በቀጠለበት ወቅት ነው። እነዚህ መነጽሮች እስካሁን ከ3.5 ቢሊዮን ዶላር በላይ ወጪ የጠየቁ ሲሆን፣ አሁንም ድረስ የብዙዎች ትችት እየቀረበባቸው ይገኛል።
Comments (0)
Join the Conversation
Share your insights and connect with other readers by signing in.



