
የiPhone 18 ከስልክ በላይ
iPhone 18 Pro በA20 Pro ቺፕ፣ ባለ 100MP ካሜራ እና በሳተላይት ግንኙነት የታጀበ ዘመናዊ ስልክ ነው። በፈጠራ የታጀበው ንድፉ፣ የላቀ AI እና ጠንካራ ባትሪው ለባለሙያዎች ተመራጭ ያደርገዋል።
ቴክኖሎጂ መረጃዎች እና በአፕል ልማዳዊ አሰራር መሰረት የiPhone 18 ተከታታይ ስልኮች ከመስከረም ወር 2019 ጀምሮ ገበያ ላይ እንደሚውሉ ይጠበቃል።
በዚህም መሰረት ከፍተኛ ጥራት ያላቸው (Premium) ሞዴሎች ( iPhone 18 Pro እና Pro Max ) በመስከረም (September) 2019 ላይ ለሽያጭ እንደሚቀርቡ ይጠበቃል። አፕል አዲሱን A20 Pro ቺፕ እና C2 ሞደም ለመጀመሪያ ጊዜ በእነዚህ ስልኮች ሥራ ላይ እንደሚያውል ይፋ አድርጔል።
መደበኛው iPhone 18 (Standard/Base Model) ሞዴሎች ግን እስከ መጋቢት 2029 እንደሚዘገዩ ይጠበቃል። ይህም የሆነው አፕል ትኩረቱን የPro ተከታታይ ሞዴሎች ሽያጭ ማሳደግ እና በታጣፊ (Foldable) ስልኮች ላይ ትኩረት በማድረጉ እንደሆነ መረጃዎች ያመላክታሉ።
ከአፕል እና በተለያዩ መንገዶች የተገኙ መረጃዎችን መሰረት በማድረግ የቴክኖሎጂ ኤክስፐርቶች እንደሚገልጹት የiPhone 18 ስልኮች :-
ንድፍ (Design)
የiPhone 18 ንድፍ ከቆይታ በኋላ ከፍተኛ ለውጥ የታየበት ነው። የአፕል ኩባንያ "All-Glass" ወይም ሙሉ በሙሉ በመስታወት የተሸፈነ የሚመስል አካል (Seamless Design) ተጠቅሟል። የጎን ፍሬሙ ይበልጥ ቀጭን እና ክብደት የሌለው የኤሮስፔስ ግሬድ ቲታኒየም (Grade 5 Titanium) ነው። ስልኩን ለየት የሚያደርገው የፊት ካሜራ እና ሴንሰሮች ሙሉ በሙሉ ከስክሪኑ ስር (Under-display FaceID) መደበቃቸው ነው፤ ይህም ሙሉ ስክሪን ብቻ እንዲታይ አድርጎታል።
ስክሪን (Display)
ባለ 6.7 ኢንች (ለPro ሞዴል 6.9) Super Retina XDR ስክሪን የተገጠመለት ነው። በሰከንድ እስከ 144Hz የማደስ ፍጥነት (Refresh rate) ያቀርባል። አዲሱ የ"Tandem OLED" ቴክኖሎጂ ስክሪኑ ከወትሮው ይበልጥ ብሩህ (እስከ 3500 nits) እንዲሆንና ጥቁር ቀለሞች እጅግ ጥልቅ ሆነው እንዲታዩ ያስችላል።
ፕሮሰሰር (Performance)
iPhone 18 በዓለማችን እጅግ ፈጣኑ በሚባለው A19 Pro ቺፕ (2nm technology) የሚሰራ ነው። ይህ ፕሮሰሰር በተለይ ለከፍተኛ የጨዋታ ግራፊክስ (Console-level Gaming) እና ለቪዲዮ ኤዲቲንግ የተሰራ ነው። ካለፈው ሞዴል በ30% ፍጥነቱ ይጨምራል።
የካሜራ ሲስተም
በካሜራ ረገድ አፕል ትልቅ እመርታ አሳይቷል፡
ዋና ካሜራ (Main): 100MP ባለ ከፍተኛ ጥራት ሌንስ።
ቴሌፎቶ (Telephoto): እስከ 10x ኦፕቲካል ዙም (Optical Zoom) የሚያደርግ የተሻሻለ ሌንስ።
Spatial Video: በ3D ጥራት ቪዲዮዎችን ለመቅረጽ እና በVision Pro ለማየት እጅግ የተመቻቸ ነው።
Apple Intelligence (AI) ~ የiPhone 18 ዋነኛ ጥንካሬ የ"Apple Intelligence" ሁለተኛ ትውልድ ነው።
Siri 2.0: አሁን Siri ከሰው ጋር እንደምናወራው አይነት የተፈጥሮ ንግግር የምትረዳ እና የስልኩን ማንኛውንም መተግበሪያ ውስጥ ገብታ ትዕዛዞችን የምትፈጽም ሆናለች።
AI Image Wand ~ በፎቶዎች ላይ ያልተፈለጉ ሰዎችን ማጥፋት ብቻ ሳይሆን፣ የጎደሉ ክፍሎችን በAI መሙላት (Generative Fill) ይችላል።
Smart Summaries ~ ረጅም ኢሜይሎችን፣ ጽሑፎችን እና የስልክ ንግግሮችን በአጭሩ አጠቃሎ ያቀርባል።
የባትሪ ዕድሜ
አዲሱ የግራፊን (Graphene) የባትሪ ቴክኖሎጂ ስልኩ ሳይሞቅ ለረጅም ጊዜ እንዲቆይ ይረዳዋል። በአማካይ አጠቃቀም እስከ 35 ሰዓታት የቪዲዮ ቆይታ እንዳለው ቢነገርም፣ በተግባር ግን ለከፍተኛ ተጠቃሚዎች ከአንድ ሙሉ ቀን በላይ (28-30 ሰዓት) ያለምንም ችግር ያገለግላል። የቻርጅ ፍጥነቱም ወደ 45W ከፍ ብሏል።
ዋጋ
አማካይ ዋጋው $2000 የአሜሪካን ዶላር አካባቢ እንደሚሆን ቢገመትም ገበያ ላይ በሚውልበት ወቅት የሚኖረውን የገበያ ዋጋ ሊወስኑ የሚችሉ ሁኔታዎች ሊያጋጥሙ እንደሚችሉም ተጠቁሟል። በተጨማሪም 256GB፣ በ512GB እና በአንድ ቴራ የሚቀርብ በመሆኑ የዋጋ ልዩነቶች እንደሚኖሩት ታውቌል።
ጉድለቶች
የጥገና ወጪ: ስልኩ ሙሉ በሙሉ በመስታወት እና በቲታኒየም የተሰራ በመሆኑ፣ ከተሰበረ የጥገና ወጪው እጅግ ከፍተኛ ሊሆን ይችላል።
AI መገደብ: አንዳንድ የላቁ የAI ባህሪያት በሁሉም ቋንቋዎች እና በሁሉም አገራት ሙሉ በሙሉ ላይሰሩ ይችላሉ።
ሙቀት: ልክ እንደ S25 Ultra ሁሉ፣ ከፍተኛ ግራፊክስ ያላቸው ጨዋታዎች ሲጫወቱ ወይም 4K ቪዲዮ ለረጅም ጊዜ ሲቀረጽ መጠነኛ ሙቀት ይታይበታል።
ማጠቃለያ
iPhone 18 ለአጠቃቀም ቀላልነትን (User-friendliness) እና ከፍተኛ ጥራት ያለው ቪዲዮ መቅረጽ ለሚፈልጉ ባለሙያዎች ተመራጭ ስልክ ነው።
Comments (0)
Join the Conversation
Share your insights and connect with other readers by signing in.


