
አፕል የመጀመሪያውን ተጣጣፊ አይፎን በ2026 ሊያስተዋውቅ ነው
አፕል ለዓመታት ሲጠበቅ የነበረውን የመጀመሪያውን ተጣጣፊ አይፎን በመጪው መስከረም 2026 ለገበያ ለማቅረብ ዝግጅቱን አጠናቋል። ይህም ለመላው ዓለም የአፕል ደንበኞቹ ትልቅ የምስራች ሆኗል።
ሚያዝያ 6፣ 2018
አፕል (Apple) ለዓመታት ሲጠበቅ የነበረውን የመጀመሪያውን ተጣጣፊ አይፎን በመጪው መስከረም ወር 2026 ለገበያ ለማቅረብ መዘጋጀቱን የBloomberg ዘግቧል።
ይህ ስልክ ከአይፎን 18 ፕሮ (iPhone 18 Pro) ተከታታይ ስልኮች ጋር በጋራ የሚተዋወቅ ሲሆን ይህም በአፕል ታሪክ ውስጥ ትልቅ የዲዛይን ለውጥ ተደርጎ የሚወሰድ ይሆናል።
እንደ ኢንዱስትሪው መረጃዎች ከሆነ አፕል ከሳምሰንግ (Samsung) ጋር በመተባበር "Self-healing" ወይም ራሱን የሚጠግን የማሳያ ሽፋን እየገነባ ነው። ይህም በተጣጣፊ ስልኮች ላይ በብዛት የሚታየውን የመታጠፊያ መስመር (crease) ችግር ይፈታል ተብሎ ይጠበቃል።
ስልኩ ልክ እንደ Samsung Galaxy Z Flip ወደ ላይ የሚታጠፍ (Clamshell) ይሁን ወይም እንደ Z Fold ወደ ጎን የሚከፈት (Book-style) እስካሁን በይፋ አልተረገጠም። ይሁንና በርካታ የዘርፉ ባለሙያዎች ወደ ጎን የሚከፈተው እና ወደ ታብሌትነት የሚቀየረውን ሞዴል እንደሚቀድም ይገምታሉ።
የስልኩ ዋጋ ከ$2,000 በላይ ሊሆን እንደሚችል ተገምቷል። ይህ ዋጋ ከመደበኛው አይፎን 18 ፕሮ ማክስ እጅግ የላቀ በመሆኑ፣ ስልኩ ለታለመላቸው ጥቂት ደንበኞች (Niche Market) ብቻ የሚቀርብ ይሆናል።
አፕል ተጣጣፊ ስልኮችን ወደ ገበያ ለማስገባት የዘገየው በማጠፊያ ክፍሎች (hinges) ጥንካሬ እና በማሳያው ጥራት ላይ ምንም ዓይነት ድርድር ማድረግ ስለማይፈልግ የላቀ ቴክኖሎጂ እስኪፈጠር ሲጠበቅ መሆኑ ታውቋል።
ለተጣጣፊ ስልኩ ተብሎ የተዘጋጀ ልዩ iOS ስሪት የመገንባት ሂደት መዘግየትም ሌላው ምክንያት እንደሆነም ተገልጿል። ይህ ሶፍትዌር ስልኩ ሲታጠፍና ሲዘረጋ ያለምንም መቆራረጥ መተግበሪያዎችን እንዲያስተካክል (Seamless transition) የሚያደርግ ነው።
ይህ እርምጃ አፕልን እንደ ሳምሰንግ፣ ጎግል እና ሁዋዌ ከመሳሰሉ ቀዳሚ የገበያ ድርሻ ያላቸው ኩባንያዎች ጋር ፊት ለፊት ለመጋጠም እንደሚያስችለው ይጠበቀል። ይሁንና ዋጋው ለብዙ ተጠቃሚዎች ተግዳሮት ሊሆን ቢችልም በሂደት የራሱን ስነ-ምህዳር በመጠቀም የተጣጣፊ ስልኮች ገበያን ሙሉ በሙሉ ሊቆጠር እንደሚችል የዘርፉ ተንታኞች ይገምታሉ።
Comments (0)
Join the Conversation
Share your insights and connect with other readers by signing in.


