
ጎግል በክሮም ብሮውሰር ላይ አዲስ ማሻሻያ አደረገ
Google በChrome Browser ላይ ‘AI Mode’ ድረ ገጾች እና የAI ውይይትን ጎን ለጎንን (Split-Screen) በማሳየት በታቦች መካከል የሚደረግ መመላለስን የሚያስቀር ዝመና አደረገ
የGoogle Chrome ‘AI Mode’ ገጹን ከፍሎ የማሳየት (Split-Screen) ባህሪን ዛሬ አስተዋወቀ።
Google በChrome መቃኛ (browser) ውስጥ በሚገኘው ‘AI Mode’ ላይ ያደረገው ከፍተኛ ማሻሻያ የAI ውይይት እና ድረ ገጾችን ጎን ለጎን በማሳየት የተቀናጀ ግለጋ ለማድረግ የሚያስችል ነው።
የተደረጉት ቁልፍ ማሻሻያዎች፦
* ጎን ለጎን ማሳየት፦ ከዚህ ቀደም ሊንኮች በአዲስ ታብ (tab) ይከፈቱ ነበር፤ አሁን ግን ተጠቃሚዎች ድረ ገጾችን ከAI ሞዱ አጠገብ በአንድ መስኮት ላይ ማየት ይቻላል። ይህም ተጠቃሚዎች የጀመሩትን የAI ውይይት ሳይለቁ ይዘቶችን ለመመርመር ያስችላቸዋል።
* የ"Tab Hopping" መቀነስ፦ ይህ ማሻሻያ ተጠቃሚዎች መረጃ ሲፈልጉ በብዙ ታቦች መካከል የሚዘዋወሩበትን (tab hopping) አድካሚ ሂደት እንደሚቀንስ Google ገልጿል።
* የማይቋረጥ የAI ረዳት፦ ቀደም ሲል አንድ ሊንክ ሲጫኑ የAI ውይይቱ ይቋረጥ ነበር፤ አሁን ግን AI ሞዱ እንደ ቋሚ ረዳት በመሆን ከጎን ክፍት ሆኖ ይቆያል። ተጠቃሚዎች ስለሚያዩት ድረ ገጽ እዚያው ጥያቄዎችን መጠየቅ ይችላሉ።
* በተለያዩ ታቦች ውስጥ መፈለግ፦ ተጠቃሚዎች አዲስ የ"Plus" ምልክትን በመጠቀም በተለያዩ ክፍት ታቦች፣ ምስሎች ወይም #PDF የመሳሰሉ ፋይሎች ውስጥ በአንድ ጊዜ መፈለግ እና መረጃዎችን ማቀናጀት ይችላሉ።
እነዚህ ማሻሻያዎች በአሁኑ ወቅት በአሜሪካ ውስጥ በኮምፒውተር እና በሞባይል ስሪቶች ላይ ዛሬ ተለቀዋል።
በሚቀጥሉት ወራት ውስጥ ደግሞ ማሻሻያው በዓለም አቀፍ ደረጃ እንደሚሰራጭ ይጠበቃል። ተጠቃሚዎች ይህንን አገልግሎት ለማግኘት ምንም አይነት ተጨማሪ ቅንብር (setup) አያስፈልጋቸውም፤ የChrome መተግበሪያቸው ሲዘምን በራሱ የሚመጣ ይሆናል።
Comments (0)
Join the Conversation
Share your insights and connect with other readers by signing in.



