የኪቦርድ አቋራጭ ቁልፎች - Keyboard Shortcuts
ቅምሻ

የኪቦርድ አቋራጭ ቁልፎች - Keyboard Shortcuts

Written byJOHN
PublishedApril 17, 2026
Read Time5 min Read

የኮምፒዩተር ኪቦርድ አቋራጭ ቁልፎች ስራን ለማቀላጠፍ እና ጊዜን ለመቆጠብ እጅግ አስፈላጊ ናቸው።  በዕለት ተዕለት የኮምፒውተር አጠቃቀምህ ላይ ትልቅ ለውጥ ያመጣሉ። ሁልጊዜ ሊጠቀሙባቸው የሚገቡ ምርጥ 15 ከታች ተዘርዝረዋል።

1. ለWin: መቅዳት Ctrl + C/Copy፣ መለጠፍ Ctrl + V/Paste, እና መቁረጥ Ctrl + X /Cut (በ Mac: Cmd + ይጠቀሙ)
ጥቅሙ: ጽሑፎችን ወይም ፋይሎችን ለመቅዳት (C)፣ ለመለጠፍ (V) እና ከአንድ ቦታ ነቅሎ ለመውሰድ ወይም ለመቁረጥ (X) ያገለግላሉ። በጽሑፍ ማቀናበሪያ "ሦስቱ ሥላሴዎች" ይበላሉ።

2. ወደ ኋላ መመለስ (Undo)
ለWin: Ctrl + Z (በ Mac: Cmd + Z)
ጥቅሙ: የሰሩትን ስህተት ወይም መጨረሻ ላይ ያከናወኑትን ድርጊት ወዲያውኑ ለመሰረዝ ይረዳል። ስህተት ሲሰሩ ምርጥ ጓደኛ ይሆንዎታል።

3. ድርጊትን መድገም (Redo)
ለWin: በስህተት "Undo" አድርጋችሁ ወደነበረበት መመለስ ስትፈልጉ Ctrl + Y (በ Mac: Cmd + Shift + Z)
ጥቅሙ: የCtrl + Z (Undo) ተቃራኒ ነው:: በስህተት የጠፋን ድርጊት መልሶ እንዲቀጥል ያደርጋል።

4. መፈለጊያ (Find)
ለWin: Ctrl + F (በ Mac: Cmd + F)ተ
ጥቅሙ: በገጽ፣ በሶፍትዌር ወይም በሰነድ ላይ የሚፈልጉትን ቃል ወይም ጽሑፍ በፍጥነት ፈልገው ለማግኘት ያስችልዎታል።

5. አዲስ ታብ (New Tab)
ለWin: Ctrl + T (በ Mac: Cmd + T)
ጥቅሙ: በብሮውዘር ላይ አዲስ የድረ-ገጽ (Tab) ወዲያውኑ ለመክፈት ያገለግላል።

6. የተዘጉ ታቦችን መመለስ (Reopen Closed Tab)
ለWin: Ctrl + Shift + T (በ Mac: Cmd + Shift + T)
ጥቅሙ: መጨረሻውን የተዘጋውን ገጽ ወዲያውኑ ይመልሳል። ድጋሚ ብትጫኑት የቀደመውን እየተከተለ ይከፍታል።

7. ወደ ዴስክቶፕ መመለስ (Go to Desktop)
ለWin: Windows Key + D (በ Mac: Mission Control ወይም F11)
ጥቅሙ: ሁሉንም የተከፈቱ መስኮቶች በአንድ ጊዜ በመሰወር ወደ ዋናው የዴስክቶፕ ገጽ ያደርስሃል።

8. በመስኮቶች መካከል መዘዋወር (Switching Tasks)
ለWin: Alt + Tab (በ Mac: Cmd + Tab)
ጥቅሙ: ክፍት የሆኑ ፕሮግራሞችን ዝርዝር ያሳይሃል፤ የሚፈልጉት ላይ ሲደርሱ በመልቀቅ በቀላሉ ይቀያይሩ።

9. ስክሪን መቆለፍ (Lock Screen)
ለWin: Windows Key + L (በ Mac: Ctrl + Cmd + Q)
ጥቅሙ: ከኮምፒውተርህ ስትነሳ መረጃህ ደህንነቱ የተጠበቀ እንዲሆን ወደ ፓስወርድ ገጽ ወዲያውኑ ይወስድሃል።

10. ስክሪን ሾት ማንሳት (Screenshot)
ለWin: Windows Key + Shift + S (በ Mac: Cmd + Shift + 4)
ጥቅሙ: ሙሉ ስክሪኑን ወይም የፈለጉትን የተወሰነ ቦታ ብቻ ፎቶ ለማንሳት ያስችላል።

11. የኢሞጂ ሰሌዳ መክፈት (Open Emoji Panel)
ለWin: Windows Key + . (ነጥብ) (በ Mac: Ctrl + Cmd + Space)
ጥቅሙ: በጽሁፎች ላይ የተለያዩ ምልክቶችን ለመጨመር እንዲቻል ዝርዝሩን ያመጣል።

12. ፋይሎችን በቋሚነት መሰረዝ (Permanent Delete) ለWin: Shift + Delete፣ ለ Mac: Option + Command + Delete
ጥቅሙ: አንድን ፋይል ወደ Recycle Bin ሳይሄድ ሙሉ በሙሉ በማጥፋት የኮምፒውተር ስቶሬጅ ለመቆጠብ ይረዳል።

13. ፋይል ስም መቀየር (Rename)
ለWin: ፋይሉን መርጠው F2፣ ለ Mac: ፋይሉን መርጠው Enter (Return) ቁልፍን ይጫኑ።
ጥቅሙ: የማውዝ ቀኝ ክሊክ (Right click) ሳይጠቀሙ የፋይል ስም ለመቀየር ፈጣኑ መንገድ ነው።

14. ብሮውዘርን ማደስ (Refresh)
ለ Win: F5 ወይም Ctrl + R፣ ለ Mac: Command + R
ጥቅሙ: አንድ የኢንተርኔት ገጽ ካልሰራ ወይም አዲስ መረጃ እንዲመጣ ሲፈልጉ ገጹን እንደገና ይጭነዋል።

15. ሁሉንም መምረጥ (Select All)
ለ Win: Ctrl + A፣ ለ Mac: Command + A
ጥቅሙ: በአንድ ገጽ ወይም ፎልደር ውስጥ ያሉትን ሁሉንም ጽሑፎች፣ ፋይሎች ወይም ምስሎች በአንድ ጊዜ ለመምረጥ ያገለግላል።

Comments (0)

Join the Conversation

Share your insights and connect with other readers by signing in.

No comments yet. Be the first to share your thoughts!