አዲሱ የአንትሮፒክ ማይቶስ ሞዴል በሀከሮች ተሰረቀ
የቴክ ዳሰሳ⭐ Featured Story

አዲሱ የአንትሮፒክ ማይቶስ ሞዴል በሀከሮች ተሰረቀ

Written byADMIN
PublishedApril 21, 2026
Read Time5 min Read

የአንትሮፒክ "ማይቶስ" AI ሞዴል በዲስኮርድ አፈትልኮ መውጣቱ ታወቀ። የደህንነት ክፍተቶችን በመለየት የሚታወቀው ይህ ቴክኖሎጂ ባልተፈቀደላቸው አካላት እጅ መግባቱ በፋይናንስ ተቋማት ላይ ከፍተኛ ስጋት ፈጥሯል።

ሰሞኑን የAi ዓለም መነጋገሪያ የነበረው "ማይቶስ (Mythos)" የተሰኘው የአንትሮፒክ አዲስ Ai ሞዴል በዲስኮርድ (Discord) በኩል አፈትልኮ መውጣቱን ብሉምበርግ ዘግቧል። 

አንድ የግል የዲስኮርድ ቡድን ያለፈቃድ አዲሱን የላቀ የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ሞዴል ( 'ማይቶስ' ) ማግኘቱን ያረጋገጠው አንትሮፒክ እንዴት ሊወጣ እንደቻለ ምርመራ እያደረገ መሆኑን አስታውቌል።

በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ በውስን መልኩ ይፋ የተደረገው ማይቶስ የደህንነት ክፍተቶችን በመለየትና ለጥቃት በማጋለጥ ረገድ ከሌሎች የ AI ሞዴሎች እጅግ የላቀ አፈጻጸም እንዳለው ታውቌል። ይሁንና ጠንቌይ ለራሱ አያውቅም እንዲሉ ራሱን ሀክ ከመደረግ መከላከል አልቻለም።

ኩባንያው ሞዴሉን በአግባቡ ባለመቆጠሩ ከፍተኛ ስጋት መፍጠሩን የጠቆመው ብሉምበርግ ባለፈው ሳምንት የአየርላንድ ብሔራዊ የሳይበር ደህንነት ማዕከል ዳይሬክተር ሪቻርድ ብራውን ቴክኖሎጂው በጥቂት ወራት ውስጥ መጥፎ ዓላማ ባላቸው አካላት እጅ ሊገባ እንደሚችል ለፓርላማ ኮሚቴ አስጠንቅቀው እንደነበር አስታውሷል።

አንትሮፒክ ሞዴሉን ለመጠቀም ፍቃድ የሰጠው አፕል፣ ጎግል፣ ማይክሮሶፍት፣ ኤንቪዲያ እና ጄፒ ሞርጋን ቼዝ ለመሳሰሉ ጥቂት የተመረጡ ኩባንያዎች እና የፋይናንስ ተቋማት ብቻ ነበር። ይህም ተቋማቱ የሳይበር ደህንነታቸውን እንዲፈትሹና እንዲያጠናክሩ ለማገዝ ታስቦ የተደረገ ነው።

የዩናይትድ ኪንግደም የፋይናንስ ተቋማት በዚህ ሳምንት ማይቶስን መጠቀም እንዲጀምሩ ታቅዶ የነበረ ሲሆን፤ ጃፓንና ካናዳም ከትላልቅ ባንኮቻቸው ጋር በጉዳዩ ላይ እየተወያዩ ነው። የአየርላንድ ባንክ (Bank of Ireland) ጉዳዩን በቅርበት እየተከታተለ መሆኑን ለSiliconRepublic.com ገልጿል።

የማይቶስ ባልተፈቀደላቸው እጅ መግባት በቴክኖሎጂው ዘርፍ ላይ ከፍተኛ ድንጋጤ የፈጠረ ሲሆን ኩባንያዎች የደህንነት ስርዓታቸውን ለማጠናከር እንዲሯሯጡ አስገድዷል። ይህ ማይቶስ የተሰኘ ሞዴል የየትኛውም መተግበሪያ ክፍተቶችን ለየት የማሳየት ከፍተኛ አቅም እንዳለው ታውቋል። መደናገጥ የተፈጠረውም ዘራፊዎች የፋይናንስ እና የደህንነት ተቋማት ክፍተቶችን በመለየት እና በክፍተቱ ሰብረው በመግባት ከፍተኛ ዘረፋ እንዳይፈጽሙ ነው።

Comments (0)

Join the Conversation

Share your insights and connect with other readers by signing in.

No comments yet. Be the first to share your thoughts!