
DeepSeek ለባለሀብቶችን አክሲዮን ለመሸጥ መነጋገር ጀመረ
የቻይናው DeepSeek ከTencent እና Alibaba ጋር እስከ 20 ቢሊዮን ዶላር በሚደርስ ግምት የኢንቨስትመንት ድርድር እያደረገ መሆኑን ገለጸ።
የቻይናው የAI ስታርትአፕ DeepSeek ተቋማዊ ዋጋውን $10 ቢሊዮን ዶላር በማስገመት ለመጀመሪያ ጊዜ የውጭ ካፒታል ማሳተፍ እንደሚፊልግ አስታወቀ። በአሁኑ ወቅትም ከTencent እና Alibaba ጋር ከ20 ቢሊዮን ዶላር በላይ በሆነ ዋጋ ድርድር እያደረገ መሆኑን አስታውቌል።
የቻይና ትላልቅ የኢንተርኔት ኩባንያዎች DeepSeekን ከድንበር ተሻጋሪ የAI ተጫዋቾች ለመጠበቅ በፍጥነት እየተንቀሳቀሱ መሆናቸው ተገልጿል።
DeepSeek ወደዓለም አቀፍ አክሲዮን እና የAI ውድድር ውስጥ መግባት የዘርፉን እድገት በከፍተኛ ደረጃ እንደሚያሳድገው ታውቋል። DeepSeek ከባድ የAi ሞዴሎችን በርካሽ መገንባት እንደሚቻል በተግባር በማሳየት ዓለም አቀፍ ትኩረት መሳብ የቻለ ስታርትአፕ መሆኑ ይታወቃል።
Tencent እና Alibaba ተሳትፎአቸውን ካጠናከሩ፣ የቻይና ቀጣይ የAI ምዕራፍ በመንግስት ፖሊሲ ብቻ ሳይሆን በሞዴል ገንቢዎች እና በፕላትፎርም ግዙፍ ኩባንያዎች መካከል በሚደረጉ ስልታዊ አጋርነቶች የሚመራ ያደርገዋል።
ምንጭ - The Information ድረገጽ
Comments (0)
Join the Conversation
Share your insights and connect with other readers by signing in.



