
ኤስኬ ሃይኒክስ የኤአይ ሚሞሪ ፍላጎት ከአቅርቦት አቅሙ በላይ መጨመሩን አስታወቀ
ኤስኬ ሃይኒክስ (SK Hynix) ለኤአይ ሚሞሪ ቺፕስ ያለው ከፍተኛ ፍላጎት ከአቅርቦት አቅሙ በላይ መድረሱን ገለጸ፤ ትርፉ በአምስት እጥፍ ማደጉ እና መሠረተ ልማቱን እያሰፋ መሆኑም አስታወቀ።
ኤስኬ ሃይኒክስ የAI ሚሞሪ ቺፕስ ፍላጎት እየጨመረ በመምጣቱ ትርፉ በአምስት እጥፍ ማደጉን አስታወቀ። ኩባንያው በሩብ ዓመቱ አፈፀም ከፍተኛ ትርፍ ማግኘቱንም ገልጿል።
Reuters እንደዘገበው የኤንቪዲያ አቅራቢ የሆነው ኤስኬ ሃይኒክስ ኩባንያ እንዳስታወቀው ኢንዱስትሪው ለከፍተኛ የመተላለፊያ ይዘት ሚሞሪ (high-bandwidth memory) ያለው ፍላጎት በአሁኑ ጊዜ ከማምረት አቅሙ በላይ ሆኗል።
ይህም የመሠረተ ልማት ፍላጎት ሊቀዘቅዝ እንደሚችል ቀደም ሲል ከነበረው ስጋት በተቃራኒ የAI ሃርድዌር ገበያው በከፍተኛ ደረጃ መጨመሩን እንደሚያመላክት ጠቁሟል። የAI እድገት አሁንም የሴሚኮንዳክተር ደረጃን እንደገና እየቀረጸ መሆኑን እንደሚያመላክትም ኩባንያው አብራርቷል።
የሚሞሪ አሁን ስልታዊ ማነቆዎችን ለመፍታት ኤስኬ ሃይኒክስ አዳዲስ አቅሞችን እያፋጠነ፣ መሠረተ ልማትን እያስፋፋ እና በከፍተኛ ፍጥነት የላቁ መሳሪያዎች ላይ ኢንቨስት እያደረገ እንደሆነም ይፋ አድርጔል።
ምንጭ፦ Reuters.
Comments (0)
Join the Conversation
Share your insights and connect with other readers by signing in.



