ዜና ቴክ

ጎግል ክላውድ የኮርፖሬት ኤአይን ለማፋጠን 750 ሚሊዮን ዶላር ፈንድ አስጀመረ

ADMIN on April 24, 2026

1 read
ዜና ቴክ

ጎግል ክላውድ ለድርጅቶች የኤአይ ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ለማፋጠን 750 ሚሊዮን ዶላር የሚሆን የድጋፍ ፈንድ ይፋ አደረገ።

ጎግል ከአዲሶቹ የTPU ቺፖቹ እና የኤጀንት መተግበሪያዎቹ ጎን ለጎን የጎግል ክላውድ ንግዶች የAI መፍትሄዎችን በፍጥነት እንዲተገብሩ ለመርዳት 750 ሚሊዮን ዶላር የሚሆን ፈንድ ይፋ አደረገ።

ፕሮጀክቱ የAI መሠረተ ልማቶች እና የስልጠና ፕሮግራሞችን ለማስፋፋት የሚደረጉ ድጋፎችን እንደሚያካትት ታውቋል። ይህም ጎግልን በAI ውህደት ውስጥ ለሚያልፉ ኩባንያዎች ቁልፍ አጋር አድርጎ እንደሚያስቀምጠው ተገልጿል።

ፈንዱ የመካከለኛ ገበያ እና የድርጅቶችን የAI መሰናክሎች ከመቀነስ ባሻገር የጎግል ክላውድ እና ሃርድዌር ፍላጎት በማነሳሳት በስነ-ምህዳሩ ውስጥ የሚገኙ የAI ስታርትአፖችን እንደሚጠቅም የBloomberg ዘገባ ያመላክታል።

A

Written by

ADMIN

Tech Analyst.

Keep Reading

ዜና ቴክ

ADMIN on August 12, 2026

OpenAI በሊኑክስ መጠቀም የሚያስችል የChatGPT መተግበሪያ አስተዋወቀ

OpenAI የሊኑክስ (Linux) ተጠቃሚዎችና ፕሮግራመሮች ሲያቀርቡት ለቆዩት ተደጋጋሚ ጥያቄ ምላሽ በመስጠት አዲስ የChatGPT ዴስክቶፕ መተግበሪያ በሙከራ ደረጃ (preview) አስተዋወቀ። ይህ መተግበሪያ ChatGPT፣ ChatGPT Work እና Codexን በዋና ዋና የሊኑክስ ስርጭቶች ማለትም Ubuntu፣ Debian እና Fedora በመሳሰሉት ላይ ለመጠቀም ያስችላል። ተቀናቃኙ Anthropic የClaude መተግበሪያን ለሊኑክስ ከለቀቀ ከአንድ ወር በኋላ OpenAI ተመሳሳይ እርምጃ በመውሰድ ገበያውን ተቀላቅሏል።

ዜና ቴክ

ADMIN on August 12, 2026

ጉግል የGemini መተግበሪያ ተጠቃሚዎቹ ቁጥር ወደ 1 ቢሊዮን መድረሱን አስታወቀ

Gemini ai መተግበሪያ ከ1 ቢሊዮን በላይ ወርሃዊ ንቁ ተጠቃሚዎቹ ያሉት 14ኛው የድርጅቱ ግዙፍ ምርት መሆኑን ጉግል አስታወቀ። በተጨማሪም በiOS ላይ 100 ሚሊዮን ተጠቃሚዎች ሲኖሩት ከChatGPT ጋርም እኩል እየተፎካከረ ይገኛል።

ዜና ቴክ

ADMIN on July 25, 2026

AgentAi የፈጸመው አነጋጋሪ ተግባር

OpenAI በተናጠል አካባቢ (isolated environment) ሲሞክረው የነበረው የAI ኤጀንት፣ የሚፈልገውን መረጃ በማጣቱ በራሱ ውሳኔ ከተወሰነበት ገደብ ወጥቶ የHugging Faceን ድረ-ገጽ በመስበር (hack በማድረግ) መረጃ ወስዷል። የOpenAI ሥራ አስፈጻሚ ሳም አልትማን ኤጀንቱ ከቁጥጥር ውጭ ሆኖ ጥቃቱን ማድረሱን አምነዋል። ይህ ክስተት የባለሙያዎችን ስጋት እንዲጨምር አድርጎታል፤ ራሳቸውን ችለው የሚሰሩ ኤአይ ኤጀንቶች አቅም ማደጉ እና ቁጥጥር ማድረግ እየከበደ መምጣቱን አመላካች ተደርጎ ተወስዷል።

Subscribe to our Newsletter

Subscribe to our email newsletter to get the latest posts delivered right to your email.

Pure inspiration, zero spam ✈️