ዜና ቴክ

ጉግል የGemini መተግበሪያ ተጠቃሚዎቹ ቁጥር ወደ 1 ቢሊዮን መድረሱን አስታወቀ

ADMIN on August 12, 2026

1 read
ዜና ቴክ

Gemini ai መተግበሪያ ከ1 ቢሊዮን በላይ ወርሃዊ ንቁ ተጠቃሚዎቹ ያሉት 14ኛው የድርጅቱ ግዙፍ ምርት መሆኑን ጉግል አስታወቀ። በተጨማሪም በiOS ላይ 100 ሚሊዮን ተጠቃሚዎች ሲኖሩት ከChatGPT ጋርም እኩል እየተፎካከረ ይገኛል።

ለጉግል (Google) ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሱንዳር ፒቻይ በX (ቀድሞ ትዊተር) ገጻቸው ዛሬ እንዳስታወቁት የGemini መተግበሪያ በከፍተኛ ፍጥነት ከሚያድጉ የድርጅቱ ምርቶች አንዱ በመሆን ንቁ ወርሃዊ ተጠቃሚዎቹ 1 ቢሊዮን አልፏል።

ፒቻይ አያይዘውም Gemini 1 ቢሊዮን ተጠቃሚዎችን ማፍራት የቻለ 14ኛው የጉግል ምርት መሆኑን ጠቁመዋል።

ይህ የGemini ፈጣን እድገት በወርሃ ሰኔ (June) ላይ 1 ቢሊዮን ወርሃዊ ንቁ ተጠቃሚዎች ላይ ከደረሰው የOpenAI ChatGPT ጋር ጎን ለጎን እየተጓዘ መሆኑን ያመላክታል።

ጉግል ከፍለጋ (Search) እና ከ-Workspace እስከ አንድሮይድ እና ለብቻው እስከሚሰራው መተግበሪያው ድረስ በተለያዩ ምርቶቹ ውስጥ Geminiን በቋሚነት ሲያዋህድ ቆይቷል። በተለይም በጉግል ፍለጋ ላይ ያለው "AI Mode" ከፍተኛ ስኬት ማስመዝገቡ ታውቋል። በዓለም ዙሪያ ከ1 ቢሊዮን በላይ ወርሃዊ ንቁ ተጠቃሚዎች አሉት።

ጉግል ዛሬው በስራ አስፈጻሚው ይፋ ያደረገው አኃዝ በተለየ ሁኔታ የGemini መተግበሪያን ብቻ የሚመለከት እንጂ ከሌሎች የጉግል አገልግሎቶች ጋር የሚጠቀሙትን እንደማያካትት ታውቋል።

ጉግል ሰዎች ቻትቦቱን በርግጥ እንዴት እየተጠቀሙበት እንደሆነ የሚያሳይ መረጃ ያጋራ ሲሆን፣ 63% የሚሆኑት የ-Gemini ተጠቃሚዎች የድምፅ (voice) ባህሪውን በመጠቀም በቀጥታ ከአሲስታንቱ ጋር እንደሚነጋገሩ ገልጿል። በተጨማሪም በጉግል መረጃ መሠረት Gemini በአሁኑ ወቅት በየቀኑ ከ150 ሚሊዮን በላይ ምስሎችን ይፈጥራል።

ጉግል አያይዞም በአሁኑ ወቅት በiOS (የአፕል ስልክ) ላይ ከ100 ሚሊዮን በላይ ንቁ ተጠቃሚዎች እንዳሉት ገልጿል።

A

Written by

ADMIN

Tech Analyst.

Keep Reading

የፕሮፕት ቋት

ADMIN on September 7, 2026

በአሁኑ ወቅት #chatgptai 📱ከስልክ ካሜራ ጋር በማገናኘት ዋና ዋና ተግባራት ማከናወን የሚያስችሉ 9 AI ትእዛዞች (Master Prompts) ከነ መግለጫቸው

🔥 የስልካችን ካሜራን ተጠቅሞ ሁሉንም አስተማሪነት፣ ትርጉም፣ ችግር ፈቺነት እና የቴክኒክ ረዳትነት ክህሎቶች አጣጥሞ ያካተተ ለማንኛውም አይነት ምስል አገልግሎት ሁለገብ መፍትሄ የሚሆኑ ትዕዛዞች (Promote)

ዜና ቴክ

ADMIN on September 7, 2026

የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ መብቶች ኮሚሽነር AI የደህንነት እና የቁጥጥር ማዕቀፎች እንዲበጁለት ጠየቁ

የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ መብቶች ኮሚሽነር ቮልከር ቱርክ AI ለሰው ልጅ ህልውና ስጋት ሊሆን እንደሚችል አስጠነቀቁ። ጥቂት ግለሰቦች በቴክኖሎጂው ላይ ያልተገደበ ስልጣን እንደያዙ በመጠቆም፣ ሁኔታው ከመባባሱ በፊት ጠንካራ የህግ እና የደህንነት ማዕቀፎች እንዲዘረጉ ጥሪ አቅርበዋል።

Subscribe to our Newsletter

Subscribe to our email newsletter to get the latest posts delivered right to your email.

Pure inspiration, zero spam ✈️