
ዜና ቴክ⭐ Featured Story
ጎግል በአንትሮፒክ እስከ 40 ቢሊዮን ዶላር ኢንቨስት ለማድረግ ወሰነ
PublishedApril 26, 2026
Read Time5 min Read
ጎግል 10 ቢሊዮን ዶላር ለአንትሮፒክ ኢንቨስት በማድረግ አጋርነቱን አጠናከረ፤ ይህም የኩባንያውን ዋጋ 350 ቢሊዮን ዶላር በማድረስ የኮምፒውቲንግ አቅሙን እንደሚያሳድገው ይጠበቃል::
🙏 የኩባንያው ዋጋም 350 ቢሊዮን ዶላር ደርሷል
ጎግል 10 ቢሊዮን ዶላር በአንትሮፒክ ላይ ኢንቨስት የሚያደርግ ሲሆን፣ ቀሪው 30 ቢሊዮን ዶላር ደግሞ በሥራ አፈፃፀም ግቦች ላይ ተመስርቶ የሚለቀቅ ይሆናል። ይህ ስምምነት የኩባንያውን አጠቃላይ ዋጋ 350 ቢሊዮን ዶላር ሲያደርሰው በሁለቱ ተቋማት መካከል ያለውን ሰፊ አጋርነትም ያጠናክራል።
አንትሮፒክ የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ሞዴሎችን የሚገነባ ኩባንያ ሲሆን፣ በተለይም ክላውድ ኮድ (Claude Code) የተሰኘው የኮዲንግ መተግበሪያው ከፍተኛ ተፈላጊነትን አግኝቷል።
በስምምነቱ መሰረት የጎግል ክላውድ (Google Cloud) ለሚቀጥሉት 5 ዓመታት እስከ 5 ጊጋ ዋት (GW) የሚደርስ የኮምፒውቲንግ አቅም ለአንትሮፒክ ያቀርባል።
ሁለቱ ኩባንያዎች በአንድ በኩል አጋር በሌላ በኩል ደግሞ ተፎካካሪ ሲሆኑ አንትሮፒክ ለሥራው የሚያስፈልጉትን ቺፖች እና መሠረተ ልማቶች ለማግኘት በጎግል ላይ ይተማመናል።
Comments (0)
Join the Conversation
Share your insights and connect with other readers by signing in.
No comments yet. Be the first to share your thoughts!


