የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ መብቶች ኮሚሽነር AI የደህንነት እና የቁጥጥር ማዕቀፎች እንዲበጁለት ጠየቁ
ADMIN on September 7, 2026
1 read
የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ መብቶች ኮሚሽነር ቮልከር ቱርክ AI ለሰው ልጅ ህልውና ስጋት ሊሆን እንደሚችል አስጠነቀቁ። ጥቂት ግለሰቦች በቴክኖሎጂው ላይ ያልተገደበ ስልጣን እንደያዙ በመጠቆም፣ ሁኔታው ከመባባሱ በፊት ጠንካራ የህግ እና የደህንነት ማዕቀፎች እንዲዘረጉ ጥሪ አቅርበዋል።
የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ መብቶች ኮሚሽነር ሰው ሰራሽ አስተውሎት ለሰው ልጅ "ህልውና" ስጋት ሊሆን እንደሚችል አስጠነቀቁ።
ኮሚሽነሩ ቮልከር ቱርክ ዛሬ እንዳስጠነቀቁት ሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) በቅርብ ጊዜያት ውስጥ የሰው ልጅ ህልውናን ለመፈታተን የሚያስችል አቅም ሊኖረው ይችላል።
“ከፍተኛ እድገት ያሳዩ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂዎች ለሰው ልጅ ህልውና ስጋት ሊሆኑ ይችላሉ በሚለው የኢንዱስትሪው ባለሙያዎች ስጋት እጋራለሁ” ሲሉም ስጋታቸውን አጠናክረዋል።
ኮሚሽነር ቮልከር ቱርክ ስጋታቸውን የገለጹት በሚቀጥለው ወር የሚጀምረውን ሁለተኛ የሥራ ዘመናቸው በማስመልከት ለተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ መብቶች ምክር ቤት ባደረጉት ንግግር ነው።
አያይዘውም “ሁኔታው ከመምሸቱ በፊት፣ በAI ደህንነት እና ጥበቃ ዙሪያ ጠንካራ እና አስተማማኝ ዋስትናዎችን ለማስቀመጥ ሙሉ ጥረት እንዲደረግ ዛሬ ጥሪ አቀርባለሁ” ብለዋል።
ስማቸውን ባይጠቅሱም "ጥቂት ግለሰቦች በAI ላይ ያልተገደበ ሥልጣን” እንደያዙ ገልጸዋል። ይሁንና ጋዜጠኞች ሜታ፣ አንትሮፒክ፣ ኦፕንኤአይ እና ጉግል የመሳሰሉ ዋና ዋና የAI ኩባንያዎች ማለታቸው እንደሆነ ጠቅሰዋል።
Written by
ADMIN
Tech Analyst.



