ዜና ቴክ

OpenAI ጂፒቲ-6 አስትራ “የትውልድ እምርታ” ማሳያ መሆኑን አስታወቀ

ADMIN on September 6, 2026

1 read
ዜና ቴክ

ኦፕንኤአይ (OpenAI) እጅግ የላቀና "አዲስ የኢንተለጀንስ ትውልድ" ያለውን "ጂፒቲ-6 አስትራ" ይፋ አደርጓል። በሳይንስ፣ ሂሳብ፣ ኮዲንግና ሳይበር ደህንነት አዳዲስ ሪከርዶችን ያስመዘገበው ይህ ሞዴል፣ በARC-AGI-3 ፈተና 99.9% ነጥብ አግኝቷል። የድርጅቱ ፕሬዚዳንት ግሬግ ብሮክማን የኤጂአይ (AGI) ዘመን መጀመሩን ገልጸዋል። የChatGPT ኤፒአይ (API) እና የAstra Pro አገልግሎቶች በጥቂት ቀናት ውስጥ እንደሚለቀቁም ጠቁመዋል።

ኦፕንኤአይ (OpenAI) ይፋ ያደረገው "ጂፒቲ-6 አስትራ" በዘርፉ የተመዘገበ የላቀ የቴክኖሎጂ እምርታ መሆኑን አስታወቀ።

ኦፕንኤአይ ከትናንት በስቲያ ይፋ ያደረገውና ለረጅም ጊዜ ሲጠበቅ የነበረው ጂፒቲ-6 አስትራ “አዲስ የኢንተለጀንስ ትውልድ” ሲል ገልጾታል።

ፕሬዚዳንቱ ግሬግ ብሮክማን (Greg Brockman) ደግሞ “እንኳን ወደ ኤጂአይ (AGI) ዘመን በደህና መጣችሁ” በማለት ገልጸውታል። ግሬግ ብሮክማን የአሜሪካ የሶፍትዌር መሐንዲስ፣ ባለሀብት እና ሥራ ፈጣሪ ሲሆኑ የታዋቂው የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) ምርምር ድርጅት የኦፕንኤአይ (OpenAI) ተባባሪ መስራች እና ፕሬዚዳንት ናቸው።

“በዓለም ላይ እጅግ ብልህ እና የተስተካከለ” የተባለው ጂፒቲ-6 አስትራ በሳይንስ፣ በሂሳብ፣ በኮምፒውተር አጠቃቀም፣ በኮርዲንግ፣ በሳይበር ደህንነት እና በሌሎችም መስኮች አዲስ የከፍተኛ ውጤት ሪከርድ አስመዝግቧል።

አስትራ በARC-AGI-3 ላይ 99.9% ነጥብ አስመዝግቧል፤ ይህም ከቀድሞው ጂፒቲ-5.6 ሶል 7.8% ከፍ ያለ ነው። በFrontierMath T4 (98%) እና በሳይበር ደህንነት ExploitBench ላይ ደግሞ 100% አስመዝግቧል።

የሚከፈልበት የChatGPT ኤፒአይ (API) በጥቂት ቀናት ውስጥ እንደሚከተል የገለጸው ድርጅቱ ድርጅቱ Astra Pro እንደሚኖርም ጠቁሟል።

የምንጭ፡ #OpenAI

A

Written by

ADMIN

Tech Analyst.

Keep Reading

የፕሮፕት ቋት

ADMIN on September 7, 2026

በአሁኑ ወቅት #chatgptai 📱ከስልክ ካሜራ ጋር በማገናኘት ዋና ዋና ተግባራት ማከናወን የሚያስችሉ 9 AI ትእዛዞች (Master Prompts) ከነ መግለጫቸው

🔥 የስልካችን ካሜራን ተጠቅሞ ሁሉንም አስተማሪነት፣ ትርጉም፣ ችግር ፈቺነት እና የቴክኒክ ረዳትነት ክህሎቶች አጣጥሞ ያካተተ ለማንኛውም አይነት ምስል አገልግሎት ሁለገብ መፍትሄ የሚሆኑ ትዕዛዞች (Promote)

ዜና ቴክ

ADMIN on September 7, 2026

የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ መብቶች ኮሚሽነር AI የደህንነት እና የቁጥጥር ማዕቀፎች እንዲበጁለት ጠየቁ

የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ መብቶች ኮሚሽነር ቮልከር ቱርክ AI ለሰው ልጅ ህልውና ስጋት ሊሆን እንደሚችል አስጠነቀቁ። ጥቂት ግለሰቦች በቴክኖሎጂው ላይ ያልተገደበ ስልጣን እንደያዙ በመጠቆም፣ ሁኔታው ከመባባሱ በፊት ጠንካራ የህግ እና የደህንነት ማዕቀፎች እንዲዘረጉ ጥሪ አቅርበዋል።

Subscribe to our Newsletter

Subscribe to our email newsletter to get the latest posts delivered right to your email.

Pure inspiration, zero spam ✈️