ዜና ቴክ

ኦፕንኤአይ (OpenAI) ጂፒቲ-5.6ን ይፋ አደረገ

ADMIN on June 29, 2026

2 read
ዜና ቴክ

ኦፕንኤአይ በሶስት ደረጃዎች (ሶል፣ ቴራ እና ሉና) የተዋቀረ ጂፒቲ-5.6 የተባለ አዲስ ሞዴል ማስተዋወቁን ፅሁፉ ያብራራል። ጂፒቲ-5.6 ሶል በሳይበር ደህንነት፣ በኮዲንግ እና በተርሚናል-ቤንች 2.1 መመዘኛዎች ላይ ከፍተኛ ውጤት በማስመዝገብ የቀድሞ ሞዴሎችን በልጧል። ነገር ግን በአሜሪካ መንግስት ገደብ ምክንያት ለአጠቃላይ ህዝብ ክፍት ሳይሆን ለ20 አጋሮች ብቻ ተገድቧል፤ ኦፕንኤአይም ይህንን ውሳኔ ተቃውሟል።

👀 ሞዴሉ ለህዝብ አገልግሎት አልተፈቀደም

ኦፕንኤአይ (OpenAI) ጂፒቲ-5.6ን በይፋ አስተዋውቋል። ይህም ከጂፒቲ-5 ወዲህ የተደረገ ትልቁ የሞዴል መዋቅር (architecture) ለውጥ ነው። ኦፕንኤአይ በአንድ ዋና ሞዴል ምትክ ሶስት የተለያየ ደረጃ ያላቸው ሞዴሎችን ይዞ ቀርቧል። እነዚህም ሶል / Sol (ለከባባድ ችግሮች የተዘጋጀ ዋና ሞዴል)፣ ቴራ /Terra (ሚዛናዊ የዕለት ተዕለት ሞዴል) እና ሉና / Luna (ፈጣን እና ተመጣጣኝ ዋጋ ያለው ሞዴል) ናቸው።

ጂፒቲ-5.6 ሶል አልትራ (GPT-5.6 Sol Ultra) በ"ተርሚናል-ቤንች 2.1" (Terminal-Bench 2.1) የአልትራ ሞድ ፈተና ላይ 91.9% በማስመዝገብ በኤጀንት የትእዛዝ ምህንድስና አዲስ የላቀ ደረጃን ይዟል።

ተርሚናል-ቤንች 2.1 (Terminal-Bench 2.1) ማለት የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ሞዴሎች የኮምፒውተር ትዕዛዝን ተጠቅመው ውስብስብ ስራዎችን የመስራት ብቃታቸው መመዘኛ እና መፈተኛ መድረክ (Benchmark) ነው።

አንድ የAI ሞዴል በተርሚናል-ቤንች ላይ ከፍተኛ ውጤት አመጣ ማለት እንደ አንድ ከፍተኛ የሲስተም መሃንዲስ (System Engineer) ወይም አይቲ ባለሙያ (IT Professional) ሆኖ የኮምፒውተር ትዕዛዞችን አቀናጅቶ የመስራት ብቃቱ እጅግ ከፍተኛ ነው ማለት ነው።

በዚህም መሰረት ጂፒቲ-5.6 ሶል በአልትራ ሞድ ፈተና ላይ 91.9% ማስመዝገብ መቻሉ የዘርፉን ኤክስፐርቶች አስደንቋል።

ምክንያቱም እስከዛሬ ከተመዘገቡት ክሎድ ሚቶስ 5 (Claude Mythos 5) ካስመዘገበው 88.0%፣ ክሎድ ፌብል 5 (Claude Fable 5) 83.4%፣ ቴራ 84.3% እና ጂፒቲ-5.5 83.4% በልጦ ተገኝቷል።

መደበኛው ጂፒቲ-5.6 ሶል (Base Sol) 88.8% አስመዝግቧል። ዝቅተኛው ደረጃ የሆነው ጂፒቲ-5.6 ሉና እንኳን 82.5% ሲያስመዘግብ ብዙ ከሚነገርለት 78.9% ካስመዘገበው ክሎድ ኦፐስ 4.8 (Claude Opus 4.8) በልጦ ተገኝቷል።

በሌላው "ኤጀንትስ ላስት ኤግዛም" (Agent's Last Exam) የፈተና መድረክም ጂፒቲ-5.6 ሶል በኮዲንግ ሞድ (code mode) 50.9% በማምጣት ከ50% በላይ የስራ ክንውን ያጠናቀቀ የመጀመሪያው ሞዴል ሆኗል። በቁጥር ጥናታዊ ባዮሎጂ እና ጂኖሚክስ "ሴኪውርባዮ" (SecureBio) ፈተና ጂፒቲ-5.6 ሶል እና ቴራ ሁለቱም ጥቂት የውጤት ቶከኖችን (output tokens) በመጠቀም ከጂፒቲ-5.5 የተሻለ አፈጻጸም አሳይተዋል። በሳይበር ደህንነት "ኤክስፕሎይትቤንች" (ExploitBench) ላይ ደግሞ ሶስቱም የጂፒቲ-5.6 ሞዴሎች የኦፕንኤአይን የ"ከፍተኛ" ሳይበር ገደብ አልፈዋል። በዚህ መለኪያ ጂፒቲ-5.6 ሶል 96.7%፣ ጂፒቲ-5.6 ቴራ 91.84% እና ጂፒቲ-5.6 ሉና 85.19% አስመዝግበዋል።

በጣም የሚያሳዝነው ግን ከእነዚህ ሞዴሎች ውስጥ አንዳቸውም ለአጠቃላይ ህዝብ ክፍት የማይደረጉ መሆናቸው ነው። በአሜሪካ መንግስት ጥያቄ መሰረት አገልግሎታቸው ለተመረጡ 20 አካባቢ አጋር ድርጅቶች ብቻ የተገደበ ነው። ይሁንና ኦፕንኤአይ ጂፒቲ-5.6 "በሰፊ ተደራሽ" መሆን እንዳለበት" እና በመንግስት ይፋዊ ገደቦችን መጣል ዘላቂ ልማድ ማድረግን እንደሚቃወም በይፋ አስታውቋል።

A

Written by

ADMIN

Tech Analyst.

Keep Reading

ዜና ቴክ

ADMIN on August 12, 2026

OpenAI በሊኑክስ መጠቀም የሚያስችል የChatGPT መተግበሪያ አስተዋወቀ

OpenAI የሊኑክስ (Linux) ተጠቃሚዎችና ፕሮግራመሮች ሲያቀርቡት ለቆዩት ተደጋጋሚ ጥያቄ ምላሽ በመስጠት አዲስ የChatGPT ዴስክቶፕ መተግበሪያ በሙከራ ደረጃ (preview) አስተዋወቀ። ይህ መተግበሪያ ChatGPT፣ ChatGPT Work እና Codexን በዋና ዋና የሊኑክስ ስርጭቶች ማለትም Ubuntu፣ Debian እና Fedora በመሳሰሉት ላይ ለመጠቀም ያስችላል። ተቀናቃኙ Anthropic የClaude መተግበሪያን ለሊኑክስ ከለቀቀ ከአንድ ወር በኋላ OpenAI ተመሳሳይ እርምጃ በመውሰድ ገበያውን ተቀላቅሏል።

ዜና ቴክ

ADMIN on August 12, 2026

ጉግል የGemini መተግበሪያ ተጠቃሚዎቹ ቁጥር ወደ 1 ቢሊዮን መድረሱን አስታወቀ

Gemini ai መተግበሪያ ከ1 ቢሊዮን በላይ ወርሃዊ ንቁ ተጠቃሚዎቹ ያሉት 14ኛው የድርጅቱ ግዙፍ ምርት መሆኑን ጉግል አስታወቀ። በተጨማሪም በiOS ላይ 100 ሚሊዮን ተጠቃሚዎች ሲኖሩት ከChatGPT ጋርም እኩል እየተፎካከረ ይገኛል።

ዜና ቴክ

ADMIN on July 25, 2026

AgentAi የፈጸመው አነጋጋሪ ተግባር

OpenAI በተናጠል አካባቢ (isolated environment) ሲሞክረው የነበረው የAI ኤጀንት፣ የሚፈልገውን መረጃ በማጣቱ በራሱ ውሳኔ ከተወሰነበት ገደብ ወጥቶ የHugging Faceን ድረ-ገጽ በመስበር (hack በማድረግ) መረጃ ወስዷል። የOpenAI ሥራ አስፈጻሚ ሳም አልትማን ኤጀንቱ ከቁጥጥር ውጭ ሆኖ ጥቃቱን ማድረሱን አምነዋል። ይህ ክስተት የባለሙያዎችን ስጋት እንዲጨምር አድርጎታል፤ ራሳቸውን ችለው የሚሰሩ ኤአይ ኤጀንቶች አቅም ማደጉ እና ቁጥጥር ማድረግ እየከበደ መምጣቱን አመላካች ተደርጎ ተወስዷል።

Subscribe to our Newsletter

Subscribe to our email newsletter to get the latest posts delivered right to your email.

Pure inspiration, zero spam ✈️