OpenAI በሊኑክስ መጠቀም የሚያስችል የChatGPT መተግበሪያ አስተዋወቀ
ADMIN on August 12, 2026
1 read
OpenAI የሊኑክስ (Linux) ተጠቃሚዎችና ፕሮግራመሮች ሲያቀርቡት ለቆዩት ተደጋጋሚ ጥያቄ ምላሽ በመስጠት አዲስ የChatGPT ዴስክቶፕ መተግበሪያ በሙከራ ደረጃ (preview) አስተዋወቀ። ይህ መተግበሪያ ChatGPT፣ ChatGPT Work እና Codexን በዋና ዋና የሊኑክስ ስርጭቶች ማለትም Ubuntu፣ Debian እና Fedora በመሳሰሉት ላይ ለመጠቀም ያስችላል። ተቀናቃኙ Anthropic የClaude መተግበሪያን ለሊኑክስ ከለቀቀ ከአንድ ወር በኋላ OpenAI ተመሳሳይ እርምጃ በመውሰድ ገበያውን ተቀላቅሏል።
OpenAI በዓለም ዙሪያ በሚገኙ የዴስክቶፕ ኮምፒውተሮች ላይ ChatGPTን ሲያስጠቅም ቢቆይም በርካታ ፕሮግራመሮች በሚገለገሉበት የሊኑክስ (Linux) ኦፕሬቲንግ ሲስተም ግን አላካተተም ነበር::
በዚህ ምክንያት የሊኑክስ ማህበረሰብ ኦፕንኤአይ የውይይት ቦቱን (chatbot) ወደ ዘርፋቸው እንዲያመጣላቸው አጥብቀው ሲጠይቁ መቆየታቸው ታውቋል።
በመሆኑም OpenAI ከትናንት ጀምሮ ለተወሰኑ የሊኑክስ ዓይነቶች የሚስማማ የChatGPT መተግበሪያ በማስተዋወቅ ለጥያቄዎች መልስ ሰጥቷል።
ድርጅቱ ዛሬ ባወጣው መግለጫ ከፍተኛ ጥያቄ ከቀረበባቸው መድረኮች የሊኑክስ ዴስክቶፕ መተግበሪያ ዋነኛው እንደነበረ አስታውቋል። ይህም ChatGPT እና Codexን በሁሉም ዋና ዋና የሊኑክስ ዴስክቶፕ ኦፐሬቲንግ ሲስተሞች ላይ መጠቀም እንደሚያስችል ገልጿል።
ይህም ማለት በሙከራ ደረጃ (preview) የተለቀቀው ይህ አዲስ መተግበሪያ የሊኑክስ ተጠቃሚዎች ChatGPT፣ ChatGPT Work እና Codexን በተለያዩ የስርዓቱ ስርጭቶች ላይ የመጠቀም እድል ይሰጣቸዋል።
መጠቀም የሚቻልባቸው የሊኑክስ ዓይነቶችም የ-Ubuntu 24.04 እና 26.04 LTS፣ የ-Debian 13 እንዲሁም የ-Fedora 43 እና 44 የዴስክቶፕ ዝርያዎችን እንደሚያካትቱ OpenAI ገልጿል።
አጠቃላይ የሊኑክስ ማህበረሰብ የሚቆጠሩ ስርጭቶችን የያዘ ቢሆንም፣
እነዚህ የተመረጡ ስርጭቶች ለተለያዩ ሌሎች የሊኑክስ ዴስክቶፕ ኦፕሬቲንግ ሲስተሞች መሰረት የሚያገለግሉ መሆናቸውን የጠቀሰው ፕሮግራመሮች መተግበሪያዎቹን አጣጥመው እንዲጠቀሙ OpenAI አስገንዝቧል።
Anthropic የዛሬ ወር አካባቢ የClaude ዴስክቶፕ መተግበሪያን ለሊኑክስ መልቀቁ የሚታወስ ሲሆን ኦፕኤአይ ጥቂት ዘግይቶም ቢሆን ተቀናቃኙን ተቀላቅሏል። የAnthropic መተግበሪያውን የለቀቀው ለUbuntu 22.04 ወይም ከዚያ በላይ እንዲሁም ለDebian 12 እና ከዚያ በላይ መሆኑ ይታወቃል።
ምንጭ - techcrunch
Written by
ADMIN
Tech Analyst.



