ዜና ቴክ

MEXC የኢትዮጵያ ብርን ከP2P (Peer-to-Peer) የግብይት ሥርዓቱ ላይ አስወገደ

ADMIN on June 10, 2026

1 read
ዜና ቴክ

ዓለም አቀፉ የክሪፕቶ መድረክ MEXC የኢትዮጵያ ብር የP2P ግብይትን ከቀጠሮው ቀድሞ በድንገት አቋርጧል። ይህም ሌሎች የክሪፕቶ ግብይት ተቋማት ያደረጉትን ማፈግፈግ ያጠናቀቀ ሆናል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በበኩሉ ጥብቅ ቁጥጥር እያደረገ ቢሆንም ደህንነቱ የተጠበቀ የዲጂታል ፋይናንስ ሥርዓት ለመፍጠር የሕግ ማዕቀፍ እያጠና ይገኛል።

ዓለም አቀፉ የክሪፕቶ ምንዛሬ መድረክ MEXC የኢትዮጵያ ብርን (ETB) ከP2P (Peer-to-Peer) የግብይት ሥርዓቱ ላይ ሙሉ በሙሉ እና በድንገትአቃረጠ።

ኩባንያው ቀደም ሲል ይህንን አገልግሎት የሚያቆመው እ.ኤ.አ. ሰኔ 30 ቀን 2026 መሆኑን ገልጾ የነበረ ቢሆንም ይፋ ባላደረገው ምክንያት ከተቀመጠው ቀነ-ገደብ ሃያ ቀናት ቀድሞ ውሳኔውን ተግብሯል።

በአሁኑ ሰዓት የኢትዮጵያ ብር (ETB) ምርጫ ከፕላትፎርሙ ላይ ሙሉ በሙሉ በማጥፋቱ አስቀድመው ዝግጅት እያደረጉ ለነበሩ የአገር ውስጥ የክሪፕቶ ተጠቃሚዎች እና ነጋዴዎች ያልተጠበቀ ድንጋጤን ፈጥሯል።

ይህ የMEXC ድንገተኛ እርምጃ በኢትዮጵያ የክሪፕቶ ገበያ ላይ የተከሰተ አዲስ ክስተት አይደለም። ከዚህ ቀደምም የአገሪቱን የፋይናንስ ሕግ እና ጥብቅ መመሪያዎችን መሠረት በማድረግ ባይናንስ (Binance)፣ ባይቢት (Bybit)፣ ቢትጌት (Bitget)፣ ኦኬኤክስ (OKX) እና ቴሌግራም ዋሌት (Telegram Wallet) የመሳሰሉ ታዋቂ ዓለም አቀፍ የክሪፕቶ መድረኮች በኢትዮጵያ ብር የሚደረጉ የP2P ግብይቶችን በተከታታይ ማቆማቸው ይታወሳል።

የMEXC ውሳኔም የክሪፕቶ የግብይት መድረኮች አሰራር ከአገሪቱ የቁጥጥር ሥርዓት ጋር ለማጣጣም የሚያደርጉትን ማፈግፈግ ሙሉ በሙሉ ያጠናቀቀ ክስተት ሆኗል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በበኩሉ ሕገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውርን ለመግታትና የፋይናንስ ሥርዓቱን መረጋጋት ለመጠበቅ ጥብቅ ቁጥጥር እያደረገ ይገኛል። ይሁን እንጂ፣ ባንኩ ከእገዳዎች ባሻገር ደህንነቱ የተጠበቀ፣ ግልጽነት እና የቁጥጥር ሥርዓት ያለው የዲጂታል ፋይናንስ ተሳትፎ በአገሪቱ መፍጠር የሚቻልበትን ሁኔታ እያጠና መሆኑን ገልጿል።

ለዚህም ይረዳው ዘንድ አጠቃላይ የቁጥጥርና የሕግ ማዕቀፍ ለማዘጋጀት ከዓለም አቀፍ አቻ ተቆጣጣሪ ተቋማት እና ከአገር ውስጥ ባለድርሻ አካላት ጋር ሰፊ ምክክርና ዝግጅት እያደረገ መሆኑን በተደጋጋሚ አስታውቋል።

A

Written by

ADMIN

Tech Analyst.

Keep Reading

የፕሮፕት ቋት

ADMIN on September 7, 2026

በአሁኑ ወቅት #chatgptai 📱ከስልክ ካሜራ ጋር በማገናኘት ዋና ዋና ተግባራት ማከናወን የሚያስችሉ 9 AI ትእዛዞች (Master Prompts) ከነ መግለጫቸው

🔥 የስልካችን ካሜራን ተጠቅሞ ሁሉንም አስተማሪነት፣ ትርጉም፣ ችግር ፈቺነት እና የቴክኒክ ረዳትነት ክህሎቶች አጣጥሞ ያካተተ ለማንኛውም አይነት ምስል አገልግሎት ሁለገብ መፍትሄ የሚሆኑ ትዕዛዞች (Promote)

ዜና ቴክ

ADMIN on September 7, 2026

የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ መብቶች ኮሚሽነር AI የደህንነት እና የቁጥጥር ማዕቀፎች እንዲበጁለት ጠየቁ

የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ መብቶች ኮሚሽነር ቮልከር ቱርክ AI ለሰው ልጅ ህልውና ስጋት ሊሆን እንደሚችል አስጠነቀቁ። ጥቂት ግለሰቦች በቴክኖሎጂው ላይ ያልተገደበ ስልጣን እንደያዙ በመጠቆም፣ ሁኔታው ከመባባሱ በፊት ጠንካራ የህግ እና የደህንነት ማዕቀፎች እንዲዘረጉ ጥሪ አቅርበዋል።

Subscribe to our Newsletter

Subscribe to our email newsletter to get the latest posts delivered right to your email.

Pure inspiration, zero spam ✈️