Lenovo ThinkCentre M90a Gen 6
የቴክ ዳሰሳ⭐ Featured Story

Lenovo ThinkCentre M90a Gen 6

Written byADMIN
PublishedMay 8, 2026
Read Time5 min Read

All-in-One ኮምፒውተር ማለት በላፕቶፕ እና በዴስክቶፕ መካከል የሚገኝ የዴስክቶፕ ትልቅ ስክሪን ከላፕቶፕ ቅልጥፍና ጋር አጣምሮ የያዘ የኮምፒውተር አይነት ነው።

አጠቃላይ ግምገማ

'ኦል-ኢን-ዋን' (All-in-One ወይም AIO) ኮምፒውተር ማለት ሁሉንም የኮምፒውተር ክፍሎች በአንድ አካል ውስጥ አጠቃልሎ የያዘ የዴስክቶፕ ኮምፒውተር አይነት ነው።

በተለመደው የዴስክቶፕ ኮምፒውተር ላይ እንደምናየው የብረት ሳጥኑ (System Unit/Tower) እና ሞኒተሩ ተለይተው አይቀመጡም። ይልቁንም ፕሮሰሰሩ (CPU)፣ ራም (RAM)፣ ሃርድ ድራይቭ እና ሌሎች የውስጥ ክፍሎች በሙሉ ከሞኒተሩ ጀርባ ተያይዘው ይገነባሉ።

በአጭሩ All-in-One ኮምፒውተር ማለት በላፕቶፕ እና በዴስክቶፕ መካከል የሚገኝ የዴስክቶፕ ትልቅ ስክሪን ከላፕቶፕ ቅልጥፍና ጋር አጣምሮ የያዘ የኮምፒውተር አይነት ነው።

በዚህ ደረጃ በቅርብ ለገበያ ከበቁት መካከል Lenovo ThinkCentre M90a Gen 6 (24″ Intel) ከፍተኛ ተቀባይነትን አግኝቷል። አብዛኞቹ 'ኦል-ኢን-ዋን' (all-in-one) ኮምፒውተሮች በብዛት የሚመረቱ በመሆናቸው በሚታዘዙበት ወቅት ዝርዝር መስፈርቶቻቸውን (specifications) ለማስተካከል ወይም ለመቀየር አያስችሉም። ይሁንና የLenovo ThinkCentre M90a Gen 6 መግዛት ለሚፈልጉ ወይም ሁሉንም ክፍሎች ከአዲሱ ትውልድ ፕሮሰሰር ጀምሮ እስከ ደጋፊ እግሩ (stand) ድረስ እንደ ምርጫቸው ለማስተካከል ሰፊ አማራጭ ማቅረቡ አቅርኗል።

በዚህም ለቢሮዎ ወይም ለስራ ቦታዎ ፍጹም ተስማሚ አቅም ያለው ኮምፒውተር መገንባት ይቻላል። ለዚህ ሞዴል ዋነኛው ማሻሻያ ወደ 14ኛው ትውልድ (14th Gen) የኢንቴል ፕሮሰሰሮች መሸጋገሩ እና የ DDR5 ራም ቴክኖሎጂን ማካተቱ ነው።

የመነሻ ሞዴሎች ተመጣጣኝ ዋጋ ቢኖራቸውም ከፍተኛ አፈጻጸም ለሚፈልጉ ተጠቃሚዎች ‘Build Your PC’ የሚለውን አማራጭ በመጠቀም የ Intel Core i5-14500 ፕሮሰሰርን ተመራጭ ሆኗል። በተለይም ኮምፒውተሩን ወደ ጎንና ወደ ላይ (portrait mode) ማዞርን ጨምሮ የተለያዩ ማስተካከያዎች ማድረግ የሚያስችለው ‘Full Function stand’ ለተጨማሪ ክፍያው በእጅጉ የሚመጥን እንደሆነ ተነግሮለታል።

የአፈጻጸም ግምገማ

ይህ ኮምፒውተር ለከፍተኛ የቢሮ ስራዎች፣ ለፕሮጀክት አስተዳደር እና ለተለያዩ ቴክኒካዊ ትንተናዎች እጅግ በጣም ተስማሚ ነው። አዲሱ የ14ኛው ትውልድ ፕሮሰሰር እና የDDR5 ራም ውህደት ከቀዳሚው Gen 5 ሞዴል ይልቅ መረጃዎችን በበለጠ ፍጥነት እንዲያስተናግድ ያስችለዋል። አፈጻጸሙ በገበያ ላይ ከሚገኙ ሌሎች ‘ኦል-ኢን-ዋን’ ኮምፒውተሮች ጋር ሲነጻጸር ግንባር ቀደም ደረጃ ላይ ይገኛል። ሆኖም ThinkCentre ራሱን የቻለ የግራፊክስ ካርድ (Dedicated GPU) ከመጠቀም ይልቅ በፕሮሰሰሩ ላይ የተገነባውን Intel UHD 770 ግራፊክስ ስለሚጠቀም ለከባድ የ3D ዲዛይን ወይም ለከፍተኛ ቪዲዮ ጌሞች ሳይሆን ለቢሮ እና ለቴክኖሎጂ ስራዎች የተወሰነ አድርጎታል።

ስክሪን እና ዲዛይን

የኮምፒውተሩ ስክሪን ጥራት ማራኪ ነው። መጠኑ 23.8 ኢንች (በተለምዶ 24 ኢንች የሚባለው) ነው፤ 1920x1080 ፒክሰል ጥራት (FHD resolution) እና የIPS ፓነል አለው። ቀለማቱ እጅግ የጠሩ በመሆናቸው ለረጅም ሰዓታት ስክሪን ለሚመለከቱ ባለሙያዎች ምቹ ነው። የብሩህነት መጠኑ ለቤት ውስጥ እና ለብርሃናማ የቢሮ አጠቃቀም ከበቂ በላይ ነው።

የግንባታ ጥራቱም የሌኖቮን የዘመናት አስተማማኝነት የጠበቀ ነው። ኮምፒውተሩ እጅግ ቀጭን የሆኑ የጎንና የላይኛው ጠርዞች (bezels) ሲኖሩት ዘመናዊ መልክ አጎናጽፈውታል። የታችኛው ክፍል ሰፋ ሲል ድምጻቸው የጠራ የ3-ዋት ስፒከሮችን እና የተሻሻለ የድረ ገጽ ካሜራን (Webcam) ይይዛል።

ዝርዝር መግለጫዎች (SPECIFICATIONS)

🖥️ ፕሮሰሰር: 14-core Intel Core i5-14500 (14th Gen)
📺 ስክሪን: 24in (23.8") 1920x1080-pixel IPS
ራም (RAM): 16GB DDR5 (በፍጥነት የተሻሻለ)
🎮 ግራፊክስ: Intel UHD Graphics 770
💾 ማከማቻ: 512GB PCIe Gen 4 SSD
🔊 ድምጽ: 2x 3W speakers
📶 ግንኙነት: Wi-Fi 6E, Bluetooth 5.3
📸 ካሜራ: 5MP / 1080p webcam (ከደህንነት መሸፈኛ ጋር)
🔌 ፖርቶች: 1x HDMI, 1x DisplayPort, 1x USB-C (3.2 Gen 2), በርካታ የUSB-A ፖርቶች፣ 1x Gigabit Ethernet, 1x SD card reader
🪟 ኦፕሬቲንግ ሲስተም: Windows 11 Pro

ማጠቃለያ: የThinkCentre M90a Gen 6 ፈጣን የ14ኛ ትውልድ ፕሮሰሰርን፣ ዘመናዊ ዲዛይንን እና ሰፊ የማስተካከያ አማራጮችን ያጣመረ ምርጥ የቢሮ እና የስራ ኦል-ኢን-ዋን ኮምፒውተር ነው። ለከፍተኛ የኮምፒውተር ጨዋታዎች ባይመችም ለዕለታዊ ቴክኒካዊ እና አስተዳደራዊ ተግባራት ግን ከበቂ በላይ ነው።

ደረጃ: በዘርፉ ገበያ ካሉት ባለው ብልጫ ★★★★★ (5 ★ ) ደረጃ ተሰጥቶታል።

Comments (0)

Join the Conversation

Share your insights and connect with other readers by signing in.

No comments yet. Be the first to share your thoughts!