የአጠቃቀም መመሪያዎች

Claude: የተሟላ መመሪያ (May 2026)

ADMIN on May 18, 2026

4 read
የአጠቃቀም መመሪያዎች

እ.ኤ.አ. በ2026 መጀመሪያ ላይ፣ አንትሮፒክ (Anthropic) ወደ 14 ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋ አመታዊ ገቢ፣ 30 ቢሊዮን ዶላር የገንዘብ ድጋፍ እንዲሁም ከAWS፣ Google Cloud፣ Microsoft እና NVIDIA ጋር ስትራቴጂካዊ አጋርነት መስርቷል። ከFortune 100 ኩባንያዎች 70% የሚሆኑት ይጠቀሙበታል። 4 ዋና ዋና ሞዴሎች ሲኖሩት Opus 4.7, Opus 4.6, Sonnet 4.6, እና Haiku 4.5.ናቸው። 1 ሚሊዮን ቶከን (የመረጃ አያያዝ አቅም) በOpus እና Sonnet እርከኖችም አለው።

1. Claude አንድ ሳይሆን 7 መተግበሪያዎች ናቸው።

* Chat (claude.ai): መደበኛ የድረ-ገጽ፣ የሞባይል እና የዴስክቶፕ የጽሑፍ መገናኛ ነው።
* Projects: ፋይሎችን በመጫን እና የጋራ መረጃን በመያዝ በክፍለ-ጊዜዎች መካከል ትውስታን የሚይዙ የስራ ቦታዎችን ያካትታል።
* Claude Code: ለፕሮግራመሮች የተዘጋጀ የትእዛዝ መስመር (CLI) መተግበሪያ ነው:: ኮዶችን ያነባል፤ ያሻሽላል እና ይጽፋል።
* Cowork: የሶፍትዌር ባለሙያዎች (ፕሮግራመር) ያልሆኑ ባለሙያዎች የተዘጋጀ የAI ምርታማነት መድረክ ነው። እንደ ፋይሎች፣ መረጃዎች እና የውጭ መተግበሪያ የመሳሰሉ ባለብዙ-ደረጃ ስራዎችን ያለ ፕሮግራም እውቀት እንዲፈጽሙ ያደርጋል።
* Plugins: እንደ ሽያጭ፣ ህግ፣ ግብይት የመሳሰሉ የስራ ዘርፎች የተዘጋጁ የችሎታ ስብስቦች።
* Connectors: እንደ Slack፣ Notion፣ Google Drive፣ Jira፣ Salesforce እና ሌሎች የመሳሰሉ ከ38 በላይ የስራ መሳሪያዎችን የሚያገናኝ ነው።
* Office Suite: በExcel፣ PowerPoint እና Word ውስጥ የሚገኝ ቅጥያ (Add-in) ነው።
---
2. በ5 ደቂቃ ውስጥ መጫን
1. የዴስክቶፕ መተግበሪያውን ለማግኘት [claude.com/download](https://claude.com/download) ይጎብኙ።
2. የዋጋ ዕቅዶች፡ ነጻ · Pro $20/ወር፣  Max $100/ወር (5× አጠቃቀም)፣ Max $200/ወር (20× አጠቃቀም) ናቸው።
3. መተግበሪያውን ከፍተው የCowork መተግበሪያን ይጫኑ።
4. አቃፊ (folder) ይምረጡ — Claude ፋይሎችን ማንበብ፣ ማስተካከል እና መፍጠር ይጀምሩ።
---
3. መጀመሪያ ሞዴሉን ይምረጡ
አንትሮፒክ በአሁኑ ወቅት Haiku 4.5 (ፍጥነት/ዋጋ)፣ Sonnet 4.6 (ሚዛናዊ) እና Opus 4.7 (ምርጥ የማመዛዘን ችሎታ) ይመክራል።
* Opus 4.7: በጣም ብልጥ እና ለጽሑፍ፣ ለጥልቅ አስተሳሰብ እና ለረጅም ጊዜ እቅድ ምርጥ ነው
* Sonnet 4.6: ለኮዲንግ፣ ለፈጣን ማጠቃለያ እና ለዕለታዊ ስራዎች ይመረጣል።
* Haiku 4.5: የፍጥነት እርከን — ለትልቅ እና ከፍተኛ መጠን ላላቸው ስራዎች ምርጥ ነው።
* Extended Thinking: Claude መልስ ከመስጠቱ በፊት በደረጃ እንዲያስብ ለማድረግ ይህ አማራጭ ቀዳሚ ነው።
---
4. የCowork አደረጃጀት
በCowork ውስጥ፣ Claude በተጠቃሚው ኮምፒዩተር በተዘጋጁ አቃፊዎች ውስጥ ፋይሎችን የማንበብ፣ የማስተካከል እና የመፍጠር ፈቃድ አለው።
* ረጅም ጥያቄዎችን ከመጻፍ ይልቅ .md (Markdown) ፋይሎችን መጠቀም የተሻለ ውጤት ያስገኛል።
* የአሰራር ዘይቤዎችን፣ ምሳሌዎችን እና ያለፉ ስራዎችን በMarkdown ፋይሎች ውስጥ ያስቀምጣል።
* የሚመከር የአቃፊ አወቃቀር:
     -  ABOUT ME — ማንነት፣ ሚና፣ ህጎች።
     -  TEMPLATES/
— እንደገና ጥቅም ላይ ሊውሉ የሚችሉ የጥያቄ ማዕቀፎች።
     -  CLAUDE OUTPUTS/` — የተጠናቀቁ ስራዎች የሚቀመጡበት።
----
5. ማገናኛዎች (Connectors)
       Settings → Connectors → Browse → Add.
    
እንደ Slack፣ Gmail፣ Google Drive፣ Notion፣ Jira፣ Salesforce፣ Microsoft 365 እና ሌሎችም ዋና ዋና መተግበሪያዎችን ያገናኛል።
---
6. ዓለም አቀፍ መመሪያዎች (Global Instructions)
     Settings → Cowork → Edit Global Instructions.
    
ምሳሌ፡ "መጀመሪያ ABOUT ME/ አንብብ። ሁሉም ስራዎች በCLAUDE OUTPUTS/ ውስጥ ይቀመጡ። ግልጽ ካልሆነ ጥያቄ ጠይቀኝ። አላስፈላጊ ማብራሪያ አትስጥ።"
---
7. Claude የሚበልጥባቸው ነገሮች

መጻፍ — ረጅም ጽሑፎችን ማርቀቅ፣ ማረም እና የቃላት አገባብ ማዛመድ (እንግሊዝኛ) - (አማርኛ ከሆነ Gemini ይጠቀሙ)
ማሰብ እና መተንተን — 1 ሚሊዮን ቶከን አቅም በመጠቀም ሙሉ የኮድ ስብስቦችን ወይም ሰነዶችን መተንተን።
* ከፋይሎችዎ ጋር መስራት — በቀጥታ በኮምፒውተርዎ ላይ ፋይሎችን ማስተናገድ።
* ትክክለኛ ጥያቄዎችን መጠየቅ — AskUserQuestion በመጠቀም ግልጽ እንዲያደርግ መጠየቅ።
* Artifacts — በቻት መስኮቱ ውስጥ ገበታዎችን፣ ቅጾችን እና የቀጥታ UI መፍጠር (ዋው የሚያስብል)
* የድረ-ገጽ ፍለጋ — አብሮ የተሰራ የቀጥታ የድረ-ገጽ ፍለጋ አለው።
---
8. Claude የማይጠቅምባቸው ነገሮች
* ፎቶ-ነክ ምስሎችን ለመፍጠር → Gemini (Banana)፣ Midjourney፣ DALL-E ወይም Imagen ይጠቀሙ። አሁን ደግሞ #ChatGPT በጣም አስደናቂ ሆናል።
* ቪዲዮ ለመፍጠር → በነጻ አጥጋቢ ባይሆኑም Google Veo ወይም Sora ይጠቀሙ።
---
9. Claude በExcel
* በስፕሬድሼትዎ ውስጥ የሚገኝ AI ነው።
* ለመጫን: Excel → Insert → Get Add-ins → "Claude by Anthropic" ብለው ይፈልጉ።
* አቋራጭ: Ctrl+Alt+C (Win) ወይም Ctrl+Option+C (Mac)።
---
10. የጥያቄ ማዕቀፍ (Prompt Template)
"I want to [TASK] so that [SUCCESS METRIC]. Read the uploaded files first. Don't execute yet. Use AskUserQuestion to clarify until we're aligned." ብላችሁ መጠየቅ ትችላላችሁ።
Key: Force Claude to ask YOU questions first. You direct; Claude executes.
Priority order: Context → Examples → Constraints & Rules → Goals.

ማስታወሻ - Claude በአማርኛ ለመጠየቅ ወይም ምላሽ ለማግኘት ተመራጭ አይደለም። መረጃው የሚፈለገው የግድ በአማርኛ ከሆነ በእንግሊዝኛ ጠይቆ ምላሹን ወደ Gemini በመውሰድ በአማርኛ ማስተርጎም ይቻላል::

A

Written by

ADMIN

Tech Analyst.

Keep Reading

ዜና ቴክ

ADMIN on August 12, 2026

OpenAI በሊኑክስ መጠቀም የሚያስችል የChatGPT መተግበሪያ አስተዋወቀ

OpenAI የሊኑክስ (Linux) ተጠቃሚዎችና ፕሮግራመሮች ሲያቀርቡት ለቆዩት ተደጋጋሚ ጥያቄ ምላሽ በመስጠት አዲስ የChatGPT ዴስክቶፕ መተግበሪያ በሙከራ ደረጃ (preview) አስተዋወቀ። ይህ መተግበሪያ ChatGPT፣ ChatGPT Work እና Codexን በዋና ዋና የሊኑክስ ስርጭቶች ማለትም Ubuntu፣ Debian እና Fedora በመሳሰሉት ላይ ለመጠቀም ያስችላል። ተቀናቃኙ Anthropic የClaude መተግበሪያን ለሊኑክስ ከለቀቀ ከአንድ ወር በኋላ OpenAI ተመሳሳይ እርምጃ በመውሰድ ገበያውን ተቀላቅሏል።

ዜና ቴክ

ADMIN on August 12, 2026

ጉግል የGemini መተግበሪያ ተጠቃሚዎቹ ቁጥር ወደ 1 ቢሊዮን መድረሱን አስታወቀ

Gemini ai መተግበሪያ ከ1 ቢሊዮን በላይ ወርሃዊ ንቁ ተጠቃሚዎቹ ያሉት 14ኛው የድርጅቱ ግዙፍ ምርት መሆኑን ጉግል አስታወቀ። በተጨማሪም በiOS ላይ 100 ሚሊዮን ተጠቃሚዎች ሲኖሩት ከChatGPT ጋርም እኩል እየተፎካከረ ይገኛል።

ዜና ቴክ

ADMIN on July 25, 2026

AgentAi የፈጸመው አነጋጋሪ ተግባር

OpenAI በተናጠል አካባቢ (isolated environment) ሲሞክረው የነበረው የAI ኤጀንት፣ የሚፈልገውን መረጃ በማጣቱ በራሱ ውሳኔ ከተወሰነበት ገደብ ወጥቶ የHugging Faceን ድረ-ገጽ በመስበር (hack በማድረግ) መረጃ ወስዷል። የOpenAI ሥራ አስፈጻሚ ሳም አልትማን ኤጀንቱ ከቁጥጥር ውጭ ሆኖ ጥቃቱን ማድረሱን አምነዋል። ይህ ክስተት የባለሙያዎችን ስጋት እንዲጨምር አድርጎታል፤ ራሳቸውን ችለው የሚሰሩ ኤአይ ኤጀንቶች አቅም ማደጉ እና ቁጥጥር ማድረግ እየከበደ መምጣቱን አመላካች ተደርጎ ተወስዷል።

Subscribe to our Newsletter

Subscribe to our email newsletter to get the latest posts delivered right to your email.

Pure inspiration, zero spam ✈️