ስፔስኤክስ የራሱን ጀፑዩ እና የኤአይ ቺፕ ለማምረት ማቀዱን አስታወቀ
ዜና ቴክ

ስፔስኤክስ የራሱን ጀፑዩ እና የኤአይ ቺፕ ለማምረት ማቀዱን አስታወቀ

Written byADMIN
PublishedApril 24, 2026
Read Time5 min Read

SpaceX የውጭ ጥገኝነትን ለመቀነስና የAI መሠረተ ልማት ባለቤት ለመሆን በIPO በሚሰበሰብ 2 ቢሊዮን ዶላር የራሱን GPU እና ቺፖችን ለማምረት ማቀዱን ይፋ አደረገ።

SpaceX በቅርቡ በሚጠበቀው የ $2 ቢሊዮን ዶላር የIPO (የአክሲዮን ሽያጭ) መጀመሪያ ላይ ለAI ፉክክር አሸናፊነት ከፍተኛ ማነቆ የፈጠሩት GPU እና የAI ቺፕ የማምረት እቅዱን ይፋ አድርጔል።

Reuters እንደዘገበው ኩባንያው ባለሀብቶች ወደ AI መሠረተ ልማት በሰፊው እንዲሳቡ የሚያደርገው ግፊት አካል የሆነው ይህ የራሱን GPU እና የAi ቺፕ የማምረት እቅድ የሚጠይቀውን "ከፍተኛ የካፒታል ወጪ" ለማሰባሰብ እንደሚያስችለው አመልክቷል።

ይህ እርምጃ በኦስቲን ከሚገኘው የኢሎን መስክ "Terafab" ራዕይ ጋር የተያያዘ ሲሆን SpaceX፣ xAI እና Tesla በውጭ አቅራቢዎች ላይ ሙሉ በሙሉ ከመታማመን ይልቅ ጥልቅ የሆነ ሴሚኮንዳክተር መገንባትን ታላሚ ያደረገ ነው።

SpaceX ለባለሀብቶች እንደገለጸው ከቀጥታ አቅራቢዎቹ ጋር የረጅም ጊዜ ኮንትራቶች እንደሌሉት እና አሁንም በሶስተኛ ወገኖች ላይ በጣም ጥገኛ ሊሆን እንደሚችል አስጠንቅቋል፣ ይህም እቅዱን ሊያዘገየው እንደሚችል ስጋቱን ገልጿል። በመሆኑም SpaceX ወደ GPU ዲዛይን እና ምርት በመግባት ከAI መሠረተ ልማት ጥገኝነት ወደ ባለቤትነት ለመሸጋገር የሚያስችል የላቀ እርምጃን ይሆናል።

ምንጭ፦ Reuters.

Comments (0)

Join the Conversation

Share your insights and connect with other readers by signing in.

No comments yet. Be the first to share your thoughts!