ኦፕንኤአይ ለአሜሪካ ኤጀንሲዎች እና ለአምስቱ አይኖች አገራት ስለ አዲሱ የሳይበር ሞዴሉ ገለጻ አደረገ
ዜና ቴክ

ኦፕንኤአይ ለአሜሪካ ኤጀንሲዎች እና ለአምስቱ አይኖች አገራት ስለ አዲሱ የሳይበር ሞዴሉ ገለጻ አደረገ

Written byADMIN
PublishedApril 24, 2026
Read Time5 min Read

OpenAI አዲሱን GPT-5.4 Cyber ሞዴል ለአሜሪካና "Five Eyes" አጋሮች ማስተዋወቁ፣ የAI ፉክክር ለብሔራዊ ደህንነትና ስትራቴጂካዊ መሠረተ ልማት ያለውን ወሳኝ ሚና የሚያሳይ ሆኗል።

OpenAI ለአሜሪካ የፌደራል ኤጀንሲዎች፣ ለክልል መንግስታት እና ለ"Five Eyes" አጋሮች ስለ አዲሱ GPT-5.4 Cyber ሞዴሉ ገለጻ ማድረጉን አስታወቀ። ኩባንያው በዋሽንግተን ገለጻ ያደረገው ለ50 የሳይበር መከላከያ ከፍተኛ ኤክስፐርቶች እና ባለስልጣናት ነው።

በገለጻውም የላቁ የAI መሳሪያዎች ከተከላካይ አካላት እጅ ወጥተው አላግባብ ጥቅም ላይ እንዳይውሉ ለመከላከል በደረጃ መዳረሻ (tiered-access) ፕሮግራም ማቅረቡን ይፋ አድርጓል። ይህም የAI ውድድር በከፍተኛ ፍጥነት ወደ ብሄራዊ ደህንነት ማደጉን የሚያመላክት ሆኗል። የአንትሮፒክ Mythos እና የOpenAI አዲስ የሳይበር ምርት ውጤታማ በሆነ መንገድ ለመንግስት የሳይበር መከላከያ አቅም ፈጥረዋል።

በአሁኑ ወቅት የAI ኩባንያዎችን በደህንነት መሠረተ ልማት፣ በዲፕሎማሲ እና በስለላ ትብብር ውስጥ የበለጠ ቀጥተኛ ሚና እንዲጫወቱ እያደረጋቸው ይገኛል።

ዘገባውን ያጋራው Axios የሳይበር ደህንነት የላቁ የAI መዳረሻዎች እንደ ስትራቴጂክ መሠረተ ልማት ሊታዩ ከሚችሉባቸው የመጀመሪያዎቹ ዘርፎች ቀዳሚ እንዳደረጋቸው አመልክቷል።

አሜሪካ፣ ዩናይትድ ኪንግደም፣ ካናዳ፣ አውስትራሊያ እና ኒውዚላንድ መሆናቸው ይታወቃል።

Comments (0)

Join the Conversation

Share your insights and connect with other readers by signing in.

No comments yet. Be the first to share your thoughts!